
የኢትዮ ሰላም የበይነ መረብ ሚዲያ መስራቹ እና በወቅታዊ ጉዳይ ትንታኔ በመስጠት የሚታወቀው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ (ቴዲ) አስፋው አመሻሹን ከእስር ተፈቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 15 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብቱን ተጠቅሞ ትንታኔ በመስጠት የሚታወቀው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው፣ የካቲት 9/2015 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረበበት ክስ ጉዳይ በ30 ሽህ ብር እንዲፈታ የተወሰነለት መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጅ ፖሊስ ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ማለቱን ተከትሎ ጉዳዩ ሲታይ ከቆዬ በኋላ የካቲት 15/2015 ከሰዓት በኋላ የከፍተኛ ፍ/ቤቱን የ30 ሽህ ብር የዋስትና ገንዘብ በማጽናት ቴዲ ከእስር እንዲፈታ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ይህን ተከትሎም ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው አመሻሹን ከእስር ተፈቶ ቤተሰቦቹን የተቀላቀለ መሆኑን አሚማ አረጋግጧል።
Source: Link to the Post