You are currently viewing የኢትዮ ሰላም የበይነ መረብ ሚዲያ መስራቹ እና በወቅታዊ ጉዳይ ትንታኔ በመስጠት የሚታወቀው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ (ቴዲ) አስፋው ፈራሚ የለም በሚል አለመፈታቱ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

የኢትዮ ሰላም የበይነ መረብ ሚዲያ መስራቹ እና በወቅታዊ ጉዳይ ትንታኔ በመስጠት የሚታወቀው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ (ቴዲ) አስፋው ፈራሚ የለም በሚል አለመፈታቱ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

የኢትዮ ሰላም የበይነ መረብ ሚዲያ መስራቹ እና በወቅታዊ ጉዳይ ትንታኔ በመስጠት የሚታወቀው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ (ቴዲ) አስፋው ፈራሚ የለም በሚል አለመፈታቱ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 10 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የኢትዮ ሰላም የበይነ መረብ ሚዲያ መስራቹ እና በወቅታዊ ጉዳይ ትንታኔ በመስጠት የሚታወቀው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ (ቴዲ) አስፋው ከሰሞኑ በፌደራል ፖሊስ መታሰሩ ይታወቃል። ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብቱን ተጠቅሞ ትንታኔ በመስጠት የሚታወቀው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው ብሄርን ከብሄር ማጋጨት እንዲሁም ከአልሸባብና ከኦነግ ሸኔ ጋር መገናኘት የሚል ክስ በፖሊስ በኩል የቀረበበት መሆኑን ጠበቃ ሰለሞን መግለጹ ይታወሳል። ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው የካቲት 9/2015 በፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ቀርቦ በ30 ሽህ ብር እንዲፈታ ወስኖ ነበር። ይህን ተከትሎም በቤተሰብ በኩል ክፍያ ተፈጽሞ መፍቻ ተይዞ ቢኬድም ከፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ በኩል ከብዙ ማጉላላት በኋላ የሚፈርም ኃላፊ የለም በሚል እንዲመለሱ ተደርጓል። በመሆኑም ፍ/ቤቱ በ30 ሽህ ብር ከእስር የፈታው ቴዎድሮስ በፖሊስ ምክንያት ከእስር አለመፈታቱን አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ከቤተሰብ ያገኘው መረጃ አመልክቷል። ከዚህ በተለዬ መልኩ ቴዎድሮስ አስፋው በፍ/ቤቱ በዋስትና እንዲፈታ የተወሰነ መሆኑ ቢታወቅም ፖሊስ የካቲት 10/2015 ከቀኑ 5 ሰዓት እስከ 7 ሰዓት ተኩል ድረስ ቤቱን የበረበረ ቢሆንም የተለዬ ነገር አለማግኘቱ ተገልጧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply