የኢትዮ-ሱዳን ወሰን ለማካለል የተደረጉ ስምምነቶች፤ የመልእክት ልውውጦች እና የሱዳኖች ትንኮሳ ምክንያት! በመልካሙ ሹምዬ ኮኮቤ  የአብን የም/ቤት አባል ፩. በ1902 እኢአ አዲስ አበባ ላይ…

የኢትዮ-ሱዳን ወሰን ለማካለል የተደረጉ ስምምነቶች፤ የመልእክት ልውውጦች እና የሱዳኖች ትንኮሳ ምክንያት! በመልካሙ ሹምዬ ኮኮቤ የአብን የም/ቤት አባል ፩. በ1902 እኢአ አዲስ አበባ ላይ…

የኢትዮ-ሱዳን ወሰን ለማካለል የተደረጉ ስምምነቶች፤ የመልእክት ልውውጦች እና የሱዳኖች ትንኮሳ ምክንያት! በመልካሙ ሹምዬ ኮኮቤ የአብን የም/ቤት አባል ፩. በ1902 እኢአ አዲስ አበባ ላይ በአፄ ሚኒሊክ እና የንጉስ ኤዱዋርድ 7ኛ ወኪል በነበረው በሌፍተናንት ኮሎኔል ጆን ሌን ሀሪንግቶን መካከል የተፈረመው ሥምምነት ሲሆን:- •በሥምምነቱ መሰረት ደንበሩ ተለይቶ ካርታ ተሰርቶለታል •የድንበሩ መነሻ ከኮር ኦሞሀጅር እስከ ጋላባት፤ ከጋላባት እስከ ጥቁር አባይ-ባሮ-ፒቦር-አኮቦ ወንዞች-መሊሌ..ከመሊሌ እስከ 6ኛው እና 35ኛው ማእረግ መገናኛ እንደሆነ ተገልጿል:: — ፪. የ1907 እኢአ በኢትዮጵያ እና እንግሊዝ(ሱዳን እና ኬኒያን በመወከል) የተደረገው ሥምምነት ሲሆን:- •እስከ ደቡብ ሱዳን፣ ኬንኒያና ኢትዮጵያ መገናኛ ድረስ ያለው ደንበር የተለየበት ነው:: — ፫. የ1972 እኢአ የተደረገው የመልእክቶች ልውውጥ(Exchange of Notes):- •የዘውድ ምክር ቤቱ ከተወያየበት በኇላ የተፈረመ ነው(በወቅቱ ምክር ቤቱ ውስጥ ድብድብ አስነስቶ ነበር):: •በሻለቃ ግዌን(Major Gwynn) የተከለለውን ወሰን በመሰረቱ(Basic acceptance of Major Gwynn line) በመቀበል ድንበሩን በድጋሚ ለማካለል(Re-demarcation) በሁለቱ ሀገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የመልእክት ልውውጥ የተፈፀመ ነው:: •የመልእክት ልውውጡ መሰረታዊ ነጥብ ሻለቃ ግዌን በተናጠል ያደረገው መካለል የ1902 እና የ1907 ስምምነቶች ጋር አብሮ እስከሄደ ድረስ ተቀባይነት እንዲኖረው ከዚያ ውጭ ሲሆን ደግሞ እንደገና እንዲካለል የተደረገ የመልእክት ልውውጥ ነው:: •ሻለቃ ግዌን ወደ ሱዳን ሙሉ በሙሉ አስገብቷቸው የነበሩት Halewa፣ Omdoga እና El Mutan የተባሉት ስልታዊ ተራራዎች በተመለከተ ደንበሩ በተራራዎቹ አናት ላይ እንዲያልፍ:: •ደንበሩ እንደገና ሲካለል ከነብስ ገበያ/ከዳግሊሽ ተራራ በስተሰሜን እና ደቡብ በሚል እንዲካለል:: በተለይ ከዳግሊሽ በስተሰሜን ያለው(ከቋራ እስከ ሰቲት) ከእርሻ እና ሰፈራ ጋር ተያይዘው ለሚነሱ ችግሮች ለሁለቱም ሀገሮች ተቀባይነት ባለው መንገድ(amicable solution እስኪሰጠው) እስኪፈታ ድረስ de facto holding and statuesque ተጠብቀው እንዲቆዩ:: •ደንበሩን ለማካለል የደንበር ኮሚሽን እንዲቋቋም እና ስራ እንዲጀምር መልእክት ተለዋውጠው የነበረ ቢሆንም የንጉሱ መንግስት በደርግ ስለተገረሰሰ ጉዳዩ ሳይገፋበት ቀርቷል:: •አንዳንድ ባለሙያዎች ይህ የመልእክት ልውውጥ በወቅቱ በነበረው ሕገ መንግስት መሰረት የፀደቀ አይደለም የሚል መከራከሪያ ያቀርቡበታል:: ፬. የ2005 እኢአ የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ(MoU) ይህ ስምምነት በኢትዮጵያ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር(አባይ ፀሃየ) እና በሱዳን የሀገር ውስጥ ሚኒስትር መካከል የተፈረመ ነው:: •ከእርሻ ሥራ፣ ሰፈራና ደንበር አካባቢ የሚከሰቱ ግጭቶች ጋር የተያያዘ ስምምነት ነው:: •”The two parties abide by their adherence to the sovereignty of each of them in their respective territories, and their commitment to the agreements concluded in 1902 and 1907 and the Exchange of Notes between the two countries in 1972 in addition to the mutually agreed upon arrangements through joint commissions.” በማለት የመግባቢያ ሰነዱ የሚገልፅ ሲሆን መሬት ቆርሶ የሚሰጥ አንቀፅ የለውም። •ከግዌን መስመር በስተምእራብ የሚያርሱ የኢትዮጵያ አርሶአደሮች እርሻቸውን እያረሱ እንዲቀጥሉ በስምምነቱ ላይ ተመልክቷል። •መሬት ላይ የሚደረገው የእኛ አርሷአደሮችን የማፈናቀል እና መሬቱን ለሱዳኖች የመስጠት ስራ ለወደፊት የሚደረገውን ማካለል ውጤት ለመወሰን በሱዳን እና በትህነግ ሰዎች የሚደረግ ሕገ ወጥ ስራ እንጅ የሰነድ መሰረት የለውም። የሻለቃ ቻርለስ ግዌን መስመር ሻለቃ ግዌን(የእንግሊዝ ወታደር እና cartographer የነበረ) በእንግሊዝ መንግሥት የተወከለ እና የደንበር መካለሉ በሁለቱ ሀገሮች የጋራ ኮሚቴ እንዲሰራ የሚደነግገውን የሥምምነቱ አካል ወደ ጎን በማለት የ1902 ሥምምነት መሰረት አድርጎ በ1903፣ የ1907 ሥምምነት መሰረት አድርጎ ደግሞ በ1909 የደንበር ማካለል (demarcation) ሥራ ብቻውን ሰርቶታል። •ድንበሩን በሶስት ከፍሎ ነው ያካለለው:: የመጀመሪያው ከሰቲት ወንዝ እስከ ሽንፋ ወንዝ ያለው ሲሆን ሁለተኛው ከሽንፋ ወንዝ እስከ አባይ ወንዝ ድረስ ያለው ነው።ሶስተኛው ከአባይ ወንዝ እስከ መሊሌ ያለው ነው። •በ1902ቱ ሥምምነት መሰረት የድንበሩ የሰሜን ጫፍ መነሻ ኮር ኦማሀጅር(ኤርትራ ውስጥ ያለ አካባቢ) ተብሎ የተጠቀሰ ቢሆንም እንግሊዝ እና ጣሊያን(Talbot/Martinelli) የኤርትራ እና ሱዳንን ደንበር ያካለሉት ከአቡገማል ሰቲት ራውያን(ኮር ሮያን) ወንዞች መገናኛ(Confluence) ላይ በመሆኑ ትንሽ ወደ ምእራብ በመሄድ የሰቲት እና ራውያን ወንዞች መገናኛ ላይ አድርጎታል። •ከልጉዲ ተራራ(ሰቲት ሁመራ) እስከ ጏንግ ወንዝ ድረስ ባለው 650km2 መሬት ከኢትዮጲያ(ሁመራ እና ምእራብ አርማጭሆ) ወደ ሱዳን አካሏል:: •ከመተማ -ጋላባት እስከ ሽንፋ ወንዝ ድረስ በታሪክ የማሕበረ ሥላሴ ገዳም መሬት መሆናቸው የሚታወቁት እጅግ ለም እና ስልታዊ ጠቀሜታ ያላቸውን Marterahed፣ Jebel Marfin፣ Tiha፣ Fazira (ግዌን የአማረኛ ስሞችን እየተወ አረበኛ ስያሜዎችን ብቻ ነው የተጠቀመው) ጨምሮ እስከ ነብስ ገበያ ድረስ ባለው ሰፊ መሬት ወደ ሱዳን አካሏል። አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ከ1902ቱ ሥምምነት በመቃረን ከ30-40 ኪሜ ድረስ ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ለሱዳን ከልሎታል። •ነብስ ገበያ/ Jebel Halewa/ዳግሊሽ፣ Omdog/Omuduga እና El Mutan/Jebel Mutan እና Jebel Jerok የተባሉቱን ስልታዊ ጠቀሜታ ያላቸው ተራራዎች በግማሽ ጨረቃ ቅርፅ እስከ 3 ኪሎሜትር ወደ ኢትዮጵያ መሬት በመግባት ወደ ሱዳን አካሏቸዋል። •ሻለቃ ግዌን በሥምምነቱ መሰረት የድንበር ወሰን ለማካለል Geography coordinates እንዲቀመጥ የሚያስገድደውን ድንጋጌ በመተው የመሬቱ አቀማመጥ አልተመቸኝም በማለት የማይታዩ እና ግልፅ ያልሆኑ የንግድ መስመሮችን፣ የወንዝ ፍሰቶችን እና የድንጋይ ቁልሎችን በመጠቀም ነው አካለልኩ ያለው።እነዚህ ምልክቶች ደግሞ ከጊዜ ብዛት እና በተለያየ ምክንያት ጠፍተዋል። በግዊን መስመር ላይ ጥናት ያደረጉት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም እንዳሉት:- “ዋናው ጥያቄ የጉዊንን የክለላ መስመር እንቀበለው? ወይስ አንቀበለው ? የሚለው አይደለም፡፡ ዋናው ጥያቄ የጉዊን የክለላ መስመር ሳይነካና ሳይለወጥ አሁንም ካለ አንድ ነገር ነው፡፡ ግን የጉዊን መስመር የሚባለው በልዩ ልዩ ምክንያቶች በልዩ ልዩ ዘዴ ተለውጦ ይገኛል፡፡” መውጫ ሱዳን ወይም ሱዳን ደንበር አካባቢ ያሉ ኃይሎች በእኛ ይዞታ ስር ያለውን መሬት ገፍተው/ወረው ለመያዝ የሚያስችል የሕግ መሰረት የላቸውም።እንዲያውም ደንበሩ ከዚህ በፊት የተደረጉ ሥምምነቶችን መሰረት አድርጎ በሁለቱም ሀገሮች ተቀባይነት ባለው መንገድ(amicable solution) እንዲፈታ እና እስኪፈታ ድረስ ማንም ከይዞታው እንዳይፈናቀል የተደረሰውን ሥምምነት የሚጥስ ነው።የሱዳኖች ጥረት ወደ ‘ድጋሚ ማካለል’ ስንገባ አንደኛው መለኪያ de facto holding and statuesque ስለሚሆን እኛ አስለቀን ይዘን ከቆየን የእኛ መሬት ተደርጎ ይቆጠርልናል ከሚል ምኞት ይመስላል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply