የኢትዮ አሜሪካ የኢንቨስትመንት ውይይት ተካሄደ

የኢትዮ አሜሪካ የኢንቨስትመንት ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮ አሜሪካ የኢንቨስትመንት ውይይት በአፍሪካ የአሜሪካ ኮርፖሬት ምክር ቤት አዘጋጅነት ተካሄደ።

ውይይቱ በቪዲዮ ኮንፈረንስ የተካሄደ ሲሆን ዋነኞችን የአሜሪካ ኮርፖሬሽኖች እና በተለያዩ የኢንዱስትሪ ዘርፎች የተሰማሩ የዳያስፖራ አባላትን ጨምሮ ከ300 በላይ ሰዎች ተሳትፈዋል።

በውይይቱ የተሳተፉት የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ እዮብ ተካልኝ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስለሚገኘው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና በመንግስት ተግባራዊ እየተደረገ ስለሚገኘው የሊበራላይዜሽን ሂደት ገለፃ አድርገዋል።

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ፍፁም አረጋም ይህን ውይይት ላዘጋጀው ለአፍሪካ ኮርፖሬት ምክር ቤት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አምባሳደሩ በቀጣይነት ተመሳሳይ ውይይቶችን ከምክር ቤቱ ጋር ለመቀጠል ያላቸውን ፍላጎት በመግለፅ የአሜሪካ ኩባንያዎች እና የዳያስፖራ አባላት በኢትዮጵያ ያለውን ትልቅ የኢንቨስትመንት እድል አንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል።

በዚህም በማምረቻ፣ እሴት በተጨመረበት የግብርና ዘርፍ፣ በጤና፣ ቱሪዝም፣ በማዕድን እና በሌሎች የኢንቨስትመንት አማራጮች ሊሰማሩ እንደሚችሉ ገልፀዋል።

The post የኢትዮ አሜሪካ የኢንቨስትመንት ውይይት ተካሄደ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply