የኢትዮ ኬንያ ቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ ተካሄደ።የአዲስ አበባ ንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ኬንያ ከሚገኘው የኬንያ ማኑፋክቸሪንግ አሶሴሽን ጋር በመተባበር የኢትዮ ኬንያ ቢዝነስ ፎ…

የኢትዮ ኬንያ ቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ ተካሄደ።

የአዲስ አበባ ንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ኬንያ ከሚገኘው የኬንያ ማኑፋክቸሪንግ አሶሴሽን ጋር በመተባበር የኢትዮ ኬንያ ቢዝነስ ፎረም  በዛሬዉ እለት ተካሂዷል።

ፎረሙ የሁለቱን ሀገራት ንግድና ኢንቨስትመንት ለማጠናከር  እንደሚያግዝ ተነግሯል፡፡
የተለያ የመንግስት አካላት፣ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ እና የንግዱ ማህበረሰብ በተገኙበት  ፎረሙ በአዲስ አበባ ተካሂዷል  ።

ኢትዮጵያ እና ኬንያ  በባህል ፣ በጂኦግራፊ እንዲሁም በታሪክ ጥብቅ ቁርኝት ያላቸው ሀገራት ናቸውም ተብሏል ።

የግሉን ዘርፍ ለማጠናከር እና በሁለቱም ሀገራት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ለማስፋፋት ከፍተኛ እድልን እንደሚፈጥርም ሰምተናል።

የኢትዮጵያ ባለሃብች  ከኬንያ ከመጡ አካላት ጋር  ለመስራት ዕድል  የሚፈጥር ነውም ተብሏል ።

በሐመረ ፍሬዉ

ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply