የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር (EDR) 63 የጭነት መኪናዎችን ማስገባቱን ገለጸ።
የኢትዮ -ጅቡቲ አክሲዮን ማህበር(EDR) ከዚህ ቀደም ሲያስገባቸው ከነበሩ የተለያዩ ምርቶች በተለየ መልኩ 63 የጭነት ተሽከርካሪዎችን አስገብቷል።
ማህበሩ ከዚህ በፊት የምግብ ዘይት፣የአፈር ማዳበሪያ ፣ብረታ ብረቶችን እና የግንባታ እቃዎችን ሲያስገባ ቆይቷል።
አሁን ደግሞ የመጀመሪያ ዙር 63 የጭነት ተሽከርካሪዎችን ያስገባ ሲሆን መኪናዎችን የማስገቢያ መርሃግብርም በእንዶዴ ባቡር ጣቢያ ተደርጓል።
የኢትዮ -ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አብዲ ዘነበ፣ ይህ ተግባር በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ከማጠናከሩ ባለፈ በትራንስፖርት ዘርፉ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ይረዳናል ብለዋል።
ተሽከርካሪዎችን በማስገባት ሂደቱ ላይ ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ የኢትዮ -ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበርን ተመራጭ በማድረጉ አመስግነዋል።
የኢትዮ -ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር(EDR) የተመሰረተበትን አምስተኛ አመቱንም እያከበረ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በመሳይ ገ/መድህን
ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos