የኢንተርናሽናል ክራይስ ግሩፕ ተንታኝ ዊሊያም ዴቪሰን የስራ ፍቃድ ታገደ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳዮች…

የኢንተርናሽናል ክራይስ ግሩፕ ተንታኝ ዊሊያም ዴቪሰን የስራ ፍቃድ ታገደ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር የኢንተርናሽናል ክራይስ ግሩፕ ሲኒየር ተንታኝ የሆነውን ዊሊያም ዴቪሰን የስራ ፍቃድ ማገዱን አዲስ ዘይቤ አረጋግጫለው ብላለች፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዛሬ በፃፈው ደብዳቤ ግለሰቡ በኢትዮጵያ እንዲሰራ ከተፈቀደለት ስራ ውጭ በሌላ ስራ ላይ ስለመሰማራቱ መረጃ ደርሶኛል ብሏል፡፡ ይህም ለውጭ ሀገር ዜጎች በሀገር ውስጥ የስራ ፍቃድ ለመስጠት የተቀመጠውን መመርያ የሚጥስ መሆኑን ገልጿል፡፡ በዚህም መሰረት ከዛሬ ጀምሮ የስራ ፍቃዱ የታገደ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ክትትል በማድረግ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱም የደብዳቤውን ግልባጭ ለጠቅላይ አቃቤ ህግ፣ ለኢንቨስትመንት ኮሚሽን ፣ ለፌደራል ፖሊስ ፎረንሲክ ምርመራ፣ የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ልኳል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply