የኢንተርኔት መዘጋት ከፍተኛ ኪሳራ ያደረሰባቸውን አገራት ዝርዝር ኢትዮጵያ ትመራለች ተባለ። በመጠናቀቀ ላይ ባለው የፈረንጆቹ 2023 የመጀመሪያ አጋማሽ በኢንተርኔት መዘጋት ምክንያት ኢትዮጵያ…

የኢንተርኔት መዘጋት ከፍተኛ ኪሳራ ያደረሰባቸውን አገራት ዝርዝር ኢትዮጵያ ትመራለች ተባለ።

በመጠናቀቀ ላይ ባለው የፈረንጆቹ 2023 የመጀመሪያ አጋማሽ በኢንተርኔት መዘጋት ምክንያት ኢትዮጵያ በመቶ ሚሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ገንዘብ አጥታለችም ተብሏል።

ይሄንን ያለው በዲሞክራሲ እና በመብቶች ጥበቃ ላይ የሚሰራው ሴንተር ፎር አድቫንስመትን ኦፍ ራይትስ ኤንድ ዲሞክራሲ ወይንም በምህፃረ ቃል ካርድ እየተባለ የሚጠራው ተቋም ነው።

ተቋሙ ለመረጃው በምንጭነት ቴክ ኔክስት የሚሰኝ በቴክኖሎጂ ዙርያ የሚሰራ ኅትመትን ጠቅሷል።

በዚሁ የጊዜ ክልል በዓለም ዙርያ በአስራ ሦስት አገራት ስድሳ አምስት ኢንተርኔትን የመጠርቀም እርምጃዎች ተወስደዋል ይላል ይህ ተቋም። ከዚህም የተነሳ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር የሚልቅ ኪሳራ አጋጥሟል።
ከፍተኛውን እጦት ያስመዘገበችው ኢትዮጵያ ስትሆን ህንድ እና ፓኪስታን ይከተላታል ተብሏል።

ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በርካታ አጋጣሚዎች የኢንተርኔት አገልግሎትን ያቋረጠች ሲሆን ይህም በመረጃ ነፃነት ተሟጋች ተቋማት ጥርስ ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል። ካለፈው ክረምት አንስቶ ግጭት ውስጥ በሚገኘው እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀበት የአማራ ክልል የኢንተርኔት አገልግሎት ከተቋረጠ ወራት ተቆጥረዋል።

በለዓለም አሰፋ
ታህሳስ 20 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply