የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የ500 ሚሊየን ብር ኢንቨስትመንት ስምምነት ተፈራረመ

ረቡዕ ኀዳር 14 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በ500 ሚሊየን ብር ካፒታል ባህርዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ገብቶ ኢንቨስትመንት ከሚጀምር ኩባንያ ጋር የውል ስምምነት ተፈራርሟል።

የውል ስምምነቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እና የፓሮን ትሬዲንግ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አበበ አስሬ ተፈራርመዋል።

500 ሚሊየን ብር ካፒታል ኢንቨስት የሚያደርገው ኩባንያው በባህርዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ 2 ሄክታር መሬት በመውሰድ በአግሮ ፕሮሰሲንግ ላይ በመሰማራት ከ1000 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል የሚፈጥር እንደሚሆን ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል።

The post የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የ500 ሚሊየን ብር ኢንቨስትመንት ስምምነት ተፈራረመ first appeared on Addis Maleda.

Source: Link to the Post

Leave a Reply