የኢጋድ ዋና ፀሃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሃይል ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

የኢጋድ ዋና ፀሃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሃይል ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዋና ፀሃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሃይል ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ጌታቸው ሽፈራውጋር ተወያዩ፡፡

በውይይቱ ወቅት በቀጠናው ሰላምና ደህንነትን ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይ መምከራቸውን ዋና ፀሃፊው አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በአቅም ግንባታ፣ በድርድርና ሽምግልና እንዲሁም ግጭቶችን አስቀድሞ ለመከላከል በትብብር መስራት በሚቻልበት አግባብ ላይም ተወያይተዋል፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞም ኢጋድ እና ተጠባባቂ ሃይሉ በቅርቡ የመግባቢያ ሰነድ እንደሚፈራረሙ ገልጸዋል፡፡

የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሃይል በቀጠናው ሰላምና ደህንነት ለማምጣት የሚሰራ ተቋም ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

The post የኢጋድ ዋና ፀሃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሃይል ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply