የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ሰራዊቱን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 26 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ እ…

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ሰራዊቱን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 26 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ እየተደረገ ያለውን አገርን የማፍረስ ሴራ በማክሸፍ አገርን የማዳን ዘመቻ ላይ ባላቸው እውቀት፣ ልምድ እና አቅም አፍራሽ ኃይሉ እስኪደመሰስ ድረስ ከአገር መከላከያ ሠራዊት ጎን እንዲሰለፉ ተጠይቋል። መስፈርቱን የሚያሟሉ የቀድሞ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት እንዲመዘገቡ ሲል ጥሪ አቅርቧል። ለአዲስ አበባ ተመዝጋቢዎች በየክፍለ ከተማቸው፤ ለክልል ተመዝጋቢዎች በየአካባቢያቸው ባሉ የቀበሌ፣ የወረዳ አስተዳደርና የፀጥታ ወይም ሚሊሻ ፅ/ቤት ድረስ በአካል በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ ብሏል። ከህዳር 01 ቀን 2014 እስከ ህዳር 15 ቀን 2014 ድረስ መመዝገብ እንደሚቻል ያስታወቀው የአገር መከላከያ ሚኒስቴር በሁሉም የምዝገባ ጣቢያዎች ዝርዝር መስፈርቶች ተለጥፈው እንደሚገኙም ጠቁሟል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply