የኢፌዴሪ ኘሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱን የ2015 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫ ዕቅድ በማቅረብ ላይ ናቸው።በ2014 በጀት ዓመት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በዲኘሎማሲያዊ ዘ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/U8Ax5G09QqqxTu2EUaT16F1Qb6nDcNPVgAyj8u0qjoICxEWfDsAvm95qh6jnVzaBB0D5zkxhEDcYjtCv8JrikpA3gKneYpn5eQ9BZU60bceGBxwZ-MSi9BSgmJnQqUbyzq4k1lRp50IjHiuPBwk4ocTorFUvl_lXkWI72T31unURWL6KDtc_SDSbVoDgGExuGhHBmNApWG5m_Jm4LS2XktFg7wN3KeS_5Ev7hjILJbDondiZ-Sfs5OX-U23Crm8iL534ixbIQug3KuNLNpYehalYISI_p2-1-viQU6iUBvT6Ta8cyM6IV8CvPto3fd4lmYvm6u4R6LSpDpKCN-6Z6A.jpg

የኢፌዴሪ ኘሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱን የ2015 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫ ዕቅድ በማቅረብ ላይ ናቸው።

በ2014 በጀት ዓመት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በዲኘሎማሲያዊ ዘርፎች ከዕቅዱ አኳያ ተስፋ ሰጪ ውጤት ያተገኙበት ቢሆንም፣ ግጭትና መፈናቀል ያልተሻገርናቸው ችግሮች መካከል በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው ብለዋል፡፡

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የነበረውን ጦርነት እንዲሁም በአንዳንድ ቦታዎች በንፁሐን ዜጐች ላይ የደረሰው የጅምላ ጭፍጨፋ በአሉታዊ ጎናቸው የሚታወሱ ብቻ ሣይሆኑ የበርካቶችን ልብ የሰበረ መሆኑንም ገልፀዋል።

መንግስት ግጭት ጨርሶ እንዲያበቃ ከማንኛውም ወገን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመደራደርና ልዩነቶችን በሠላምና በውይይት ለመፍታት ሀሳብ ማቅረቡን ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ አስታውሰው፣ ይህንን ዕድል ስለ ትግራይ ሕዝብ ሲል ህወሃትም የሠላም ጥሪውን በመቀበል ለድርድር እንዲቀመጥ የቀረበውን ጥሪ ማክበር እንደሚገባው አሣስበዋል፡፡

መንግስት ማንኛውንም አይነት ልዩነቶችን በመነጋገር መፍታት አስፈላጊ መሆኑን በማመን ያለቅድመ ሁኔታ ለመወያየት አሁንም ጥሪውን ያቀርባልም ነዉ ያሉት፡፡

መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply