የኤም-23 አማጽያን በተስማሙት መሰረት ከያዟቸው አካባቢዎች አልወጡም ሲሉ የኮንጎ ፕሬዚዳንት ተናገሩ

https://gdb.voanews.com/022a0000-0aff-0242-b939-08dae74d99eb_w800_h450.jpg

“ኤም-23 የተባለው አማጺ ቡድን ከያዛቸው የምስራቅ ኮንጎ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ አልወጣም። ተዋጊዎቼን እስወጥቻለሁ የሚለው ውሸቱን ነው” ሲሉ የዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ቲሼኬዲ ተናገሩ።

በቱትሲዎች የሚመራው ታጣቂ ቡድን በቅርብ ጊዜ ከያዛቸው የምስራቅ ኮንጎ አካባቢዎች እስከአለፈው ሰኞ የአውሮፓውያን ጥር 15 ቀን ለቅቆ እንዲወጣ ባለፈው ህዳር በአካባቢው ሀገሮች መሪዎች ሽምግልና ተስማምቶ እንደነበር ተገልጿል።

የኮንጎ ፕሬዚዳንት ቲሼኬዲ በዳቮስ የዓለም ኢኮኖሚ ጉባዔ ላይ በሰጡት ቃል “ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ የተደረገበት ቢሆንም ታጣቂው ቡድን አሁንም አልወጣም” ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply