የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው

የኢትዮጵ ኤርትራ ወዳጅነትን ለማደስ ከሚ/ር ዐቢይ አሕመድ በቀረበላቸው ግብዣ መሠረት ከአምስት ዓመት በፊት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ወዳጅ የሆኑት፤ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ተሰምቷል፡፡

የኤርትራው ፕሬዝደንት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ያስታወቁት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ ደኅንናት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ሲሆኑ፤ አምባሳደሩ የትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፕሬዝደንቱ በቅርብ ቀን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ጠቁመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ባሳለፍነው ረቡዕ ሐምሌ 5/2015 ካይሮ ላይ በሱዳን ጉዳይ ከሱዳን ጎረቤት አገራት ጋር ለመምከር በተገናኙበት መድረክ ውይይት ማድረጋቸው ተሰምቷል፡፡

ኹለቱ መሪዎች በተገናኙበት ወቅት በሱዳን እየተደረገ ስላለው የእርስ በርስ ግጭት በዘለለ ስለ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ መጻኢ ሁኔታ ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን፤ እንዲሁም ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ውይይቱን እንደሚቀጥሉ ሬድዋን አሳቀውዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ወደ ስልጣን መምጣትን ተከትሎ፤ ከኹለት አስርት ዓመታት በላይ  ተቋርጦ የቆየውን የኢትዮ ኤርትራን ግንኙነት፤ ከአምስት ዓመት በፊት መታደሱን ተከትሎ የኹለቱ አገራት መሪዎች በየተራ ተገባብዘው ጉብኝት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡

የአሁኑ የኤርትራ ፕሬዝደንት ጉብኝት የኤርትራ ጦር ከተከሰሰበት ከሰሜኑ ጦርነት መቀስቀስ በኋላ፤ የመጀመሪያ ጉብኝታቸው ነው፡፡ በተለይ በግንኙነቱ መታደስ ወቅት በኹለቱ አገራት መሪዎች መካከል ሽር ጉድ የበዛበት ግንኙነት ነበራቸው፡፡

ይሁን እንጂ ኹለቱ አገራት ሰላም አውርደዋል ከሚለውና ከመሪዎቹ የእርስ በእርስ ግንኙነት በዘለለ፤ ስምምነቱን የሚያጸና በግልጽ የሚታይ ስምምነት በፊርማ ደረጃ አለማኖራቸ ጥያቄ ሲነሳበት ቆይቷል፡፡ “የኹለቱ አገራት ግንኙነት በመርህ ላይ የተመሰረተ አይደለም” የሚል ጥያቄ ካለሱት አካላት መካከል የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንዱ ነው፡፡

የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት ተቋማዊነትና ዘላቂነት ላይ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ የቀረበበት በ2014 ሲሆን፤ በወቅቱ ከምክር ቤት ምላሽ የሰጡጥ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፤ “የተከፈተው የሰላም በር በሚፈለገው ልክና ሊኖረን ከሚገባው ትብብር አኳያ የሚፈለገውን ያህል አድጓል ብሎ መውሰድ አይቻልም” ማለታቸውን አዲስ ማለዳ ዘግባ ነበር፡፡

የወቅቱን ሁኔታ ብዙዎች እርስ በእርስ ለጦርነት የሚፈላለጉ ጎረቤት አገራት ከነበሩበት የመጠባበቅ ኹኔታ ወጥተው ወደ ሰላማዊ ግንኙነት መምጣታቸው ትልቅ እርምጃ ወስደውት ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ግንኙነቱ በስምምነት መርህ የተመራ አልመሆኑ ከሚስነሳው ጥያቄ በተጨማሪ፣ የፌደራል መንግሥቱ ከሕወሓት ጋር ስምምነት ማድረጉን ተከትሎ በኹለቱ አገራት ግንኙነት ላይ ስጋቶች ይነሳሉ፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply