
ከኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ጎን ሆኖ የትግራይ ኃይሎችን ሲወጋ የነበረው የኤርትራ ሠራዊት ከቆየባቸው ተለያዩ ትግራይ አካባቢዎች እየወጣ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግሩ። ቢቢሲ በሽረ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎችን አናግሮ መረዳት እንደቻለው ለወራት በከተማዋ የቆዩት የኤርትራ ሠራዊት አባላት እየወጡ ናቸው። ሮይተርስ የዜና ወኪልም ሦስት ነዋሪዎች ነግረውኛል ብሎ እንደዘገበው ከሆነ የኤርትራ ሠራዊት ከሽረ እንዳሥላሴ እና አክሱም ከተሞች ወጥተዋል።
Source: Link to the Post