
የኤርትራ ሠራዊት ይገኝበት ከነበረው የአድዋ እና የአክሱም አካባቢዎች በብዛት እየወጣ መሆኑን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገለፁ። ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ በበርካታ መኪኖች የተጫኑ የኤርትራ ሠራዊት አባላት ከእንዳባገሪማ አካባቢ በመምጣት አድዋን አቋርጠው ሲያልፉ ማየታቸውን አንድ የከተማዋ ነዋሪ ለቢቢሲ ገልፀዋል። “ከዛሬ ጠዋት [ጥር 12/2015 ዓ.ም.] ጀምሮ ወታደሮቹ በጣም ብዙ በሆኑ ትላልቅ ስካንያ አውቶቡሶች፣ በሲኖትራኮች፣ በአይሱዙዎች ተጭነው ሲወጡ አርፍደዋል።”
Source: Link to the Post