የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ስርጭት በአዲስ አበባ አሁንም ድረስ በወረርሺኝ ደረጃ ላይ መሆኑ ተገለፀ፡፡

አንዲት ሀገር የቫይረሱ ስርጭት ወረርሺኝ ሆኖባታል የሚባለው የስርጭቱ መጠን ከአንድ በመቶ በላይ ሲሆን እንደሆነ የአለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡ኢትዮጵያም በሀገር አቀፍ ደረጃ ወረርሺኝ ላይ ባትሆንም ከክልል ክልል የስርጭት መጠኑ ይለያያል ተብሏል፡፡መዲናችን አዲስ አበባም 3 ነጥብ 2 በመቶ የኤች.አይ.ቪ ኤድስ የስርጭት መጠን በመያዝ ከጋምቤላ ክልል በመቀጠል በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

የአዲስ አበባ የኤች.አይ.ቪ. ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ጽህፈት ቤት የፕሮግራም አስተባባሪ ሲስተር ፈለቀች አንዳርጌ ለአሐዱ እንደገለፁት ያለፉት 3 እና 4 ዓመታት ያለው የስርጭት ሁኔታ ወረርሺኝ የሚባልበት ደረጃ ላይ የደረሰ ነው፡፡ከ20 ዓመታት ወዲህ የተወሰዱ እርምጃዎችና የተገኙ ውጤቶች ቢኖሩም ከዚያ በኃላ ግን በማህበረሰቡ ዘንድ ያለው መዘናጋት ለቫይረሱ በዚህ ልክ መስፋፋት ትልቅ ምክንያት ሆኗል ብለዋል፡፡የፀረ ኤች.አይ.ቪ. ኤድስ መድኃኒት አቅርቦት መኖር እና የሟቾች ቁጥር መቀነስ ኅብረተሰቡ ቫይረሱ ጠፍቷል ወደሚል አስተሳሰብ ውስጥ እንዲገባ እንዳደረገው ሲስተር ፈለቀች ለአሀዱ ተናግረዋል፡፡ችግሩን ለመቅረፍ ምን ሊሰራ ታስቧል ሲል አሐዱ ለአስተባባሪዋ ላነሳላቸው ጥያቄ ትብብር ትልቁ አማራጭ ነው ብለዋል፡፡ ከችግሩ አስከፊነት አንፃር የጋራ ኃላፊነት ወስዶ መወጣት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

ቀን 14/ 03/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply