የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ ማሻሻያ ተደርጓል፡፡የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ ማሻሻያ መደረጉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 ከየካቲት 5/2012…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/dF7vHwH4SB-jwqoT-nMXf0un4pguQ5lfsFcPeTmmm1x1SKJu1SMznD5RRahtvgx_Mc6pPbSolzwjweCcfE3dXBoAVsWgHnMeN_s5EenTVeymmqNjafSuj5rn_Zh2ATwr4Sx6o6gKNTKoTYBJ_M8dtzEbcM-cxntFr3MuJr23N48yo4JzRWNII1EAYd5zOjG1U9vOff5cUDYlXuiY1N8I7uHv_wJ_4dXpxBlcSxguzo2bqgzjM4h7nX65FDuCTK98xdZtBk1-8lt5HtbPR5TtofPa3pr61tnAGM-XE7zU5cQ2J4xORSQSbG4tvuu13I3qf-1uPBZpPd4w9F2dCNsCBg.jpg

የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ ማሻሻያ ተደርጓል፡፡

የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ ማሻሻያ መደረጉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።

የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 ከየካቲት 5/2012 ጀምሮ ሥራ ላይ የዋለ ሲሆን፤ ይህ አዋጅ የታክሱን መሰረት በማስፋት እና የታክሱን አስተዳደር ስርዓት በመቀየር ከፍተኛ ጠቀሜታን ማስገኘቱን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዚያ 19/2015 ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ጉባኤው በአዋጁ ላይ የቀረቡ ማሻሻያዎችን ታሳቢ በማድረግ የአዋጁ ማሻሻያ መድረጉንም ሚኒስቴሩ አስታውሷል።

የአዋጁ ማሻሻያ ታሳቢ ያደረገው ተደራራቢ የኤክሳይዝ ታክስ የተጣለባቸው ምርቶች ላይ ማሻሻያ ለማድረግ፣ በቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ላይ የኤክሳይዝ ታክስ እንዲከፈል ለማድረግ፣ የኤክሳይዝ ታክስ ተጥሎባቸው የነበሩት አንዳንድ ምርቶች ላይ ታክሱን ለማንሳት መሆናቸው ተገልጿል።

በመሆኑም ገቢዎች ሚኒስቴር የአዋጁ ማሻሻያ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውል እንዲደረግ እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት፤ የንግዱ ማህበረሰብ ሁሉ እንዲያውቁት መመሪያ ተሰጥቷል ተብሏል።

 የተደረገው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ማሻሻያ ከሥር ተያይዟል፤

Source: Link to the Post

Leave a Reply