You are currently viewing የኤፍራታና ግድም ፣ የአጣዬ እና የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር አመራሮች እና የፀጥታ አካላት ወራሪውን የህዋሃት ጁንታና ተስፋፊውን የኦነግ ሽኔን ጥቃት ለመመከት በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ ገለጹ…

የኤፍራታና ግድም ፣ የአጣዬ እና የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር አመራሮች እና የፀጥታ አካላት ወራሪውን የህዋሃት ጁንታና ተስፋፊውን የኦነግ ሽኔን ጥቃት ለመመከት በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ ገለጹ…

የኤፍራታና ግድም ፣ የአጣዬ እና የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር አመራሮች እና የፀጥታ አካላት ወራሪውን የህዋሃት ጁንታና ተስፋፊውን የኦነግ ሽኔን ጥቃት ለመመከት በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ ገለጹ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የኤፍራታና ግድም ፣ የአጣዬ እና የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር አመራሮች እና የፀጥታ አካላት ወራሪውን የህዋሃት ጁንታና ተስፋፊውን የኦነግ ሽኔን ጥቃት በመመከት በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጨረሻ ግብዓተ መሬታቸውን ለማጠናቀቅ በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ ገልጸዋል። የኤፍራታና ግድም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰሎሞን አልታዬ ፣ የአጣዬ ከተማ አስተዳር ከንቲባ አቶ አገኘሁ መክቴ እና የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ዘነበ ተክሌ የአካባቢያቸውን ነባራዊ ሁኔታ አስመልክተው አስተያዬታቸውን ሰጥተዋል። ኃላፊዎቹ በሰጡት አስተያዬትም ሕዝባችንን ደጀን በማድረግ ከመላው የፀጥታ መዋቅር ጋር በመቀናጀት በአሸባሪዎቹ ህዋሃትና ኦነግ ሽኔን የተከፈተብንን ጥቃት በመመከት ዳግም እንዳያንሰራሩ ለማድረግ በሥነ ልቡና ፣ በሰው ኃይል ፣በትጥቅና ስንቅ በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን በከፍተኛ ወኔ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። ለኦሮሞ ማኅበረሰብ ተቆርቋሪ ይመስል የነበረው ኦነግ ሽኔ ከህዋሃት ጋር በመቀላቀል በፈጸመው ጥቃት ለአማራሩና ለሕዝቡ ሥጋት መሆኑን በመረዳት የአማራና የኦሮሞ ብሔረሰብ ሕዝቦች በጋራ እየተዋጉት መሆኑን አቶ ሰሎሞን አልታዬ ተናግረዋል። ከንቲባ አገኘሁ መክቴ ደግሞ ኦነግ ሽኔ በአካባቢያችን መሸጎ እንዳይንቀሳቀስ ሰፊ ሥራ መሠራቱን ገልጸው የህዋሃትንና የኦነግ ሽኔን ጥቃት ለመመከት ከመቼውም ጊዜ በላይ በየደረጃው የሚገኘው ማኅበረሰብ በአንድነትና በትብብር የቆመበት ወቅት መሆኑን አንስተዋል። የሸዋ ሮቢት ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ዘነበ ተክሌ በበኩላቸው የክተት አዋጁ ከወጣ ጀምሮ የሥጋት ቦታዎች እየተጠበቁ ሲሆን በሁሉም ዘርፎች የሕዝቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠሉንና በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ወደ ግንባር በመዝመት ላይ እንደሚገኙና ለዘመቻውም ከፍተኛ መነሳሳት መፈጠሩን አብራርተዋል። በሁለቱም ከተማ አስተዳደሮችና በኤፍራታና ግድም ወረዳ አካባቢቸውን በንቃት ሲጠብቁ ያገኘናቸው ወጣቶች የሚከፈለውን መስዋእትነት ሁሉ በመክፈል ሁለቱንም አሸባሪዎች በመደምሰስ አካባቢያቸውንና ሀገራቸውን ከጸጥታ ሥጋት ነጻ ለማድረግ ከመቼውም ጊዜ በላቀ መልኩ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል ሲል የእንሳሮ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply