“የእርዳታው እንቅስቃሴው እንዳይፋጠን እንቅፋት የፈጠረው ህወሓት ነው” የሰላም ሚኒስቴር

https://gdb.voanews.com/38806D16-DFF0-4764-AC48-A2BAD8B69D7F_cx17_cy0_cw81_w800_h450.jpg

ከተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔው ወዲህ የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ ትግራይ ክልል ከ500 በላይ የጭነት ተሽከርካሪዎች ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ የእርዳታ ቁሳቁሶችን መላኩን የሰላም ሚኒስቴር አስታውቋል። “የእርዳታው እንቅስቃሴው እንዳይፋጠን እንቅፋት የፈጠረው ህወሓት ነው” ብሏል ሚኒስቴሩ።

ከበባ ውስጥ መሆኑን የሚናገረው ህወሓት በበኩሉ “የትግራይ ሕዝብ የእርዳታ እህል እንዳያገኝ መንግሥት እንቅፋት እየተፈጠረ ነው” ይላል።

በሌላ በኩል “አንዳንድ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መንግሥት በአሸባሪነት ለሰየመው ኃይል የጦር መሣሪያ ሲያቀብሉ መያዛቸውን”ም የሰላም ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply