የእሳት አደጋው ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል!

በድሬዳዋ አሸዋ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የእሳት አደጋ ደርሶ ነበር፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር እና የካቢኔ አባላት እንዲሁም የአስተዳደሩ አመራር አካላት አደጋው በደረሰበት ስፍራ ተገኝተው ተመልክተዋል።

ዛሬ ከማለዳው አንድ ሰዓት አካባቢ ጀምሮ የተከሰተውን የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ለማዋል ከፍተኛ ጥረት መደረጉን ከንቲባ ከድር ጁሃር ተናግረዋል፡፡

በተከሰተው ድንገተኛ አደጋ ሀብት እና ንብረት የተጎዳባቸው ወገኖችን ለመደገፍ አስተዳደሩ መላውን ህብረተሰብ በማስተባበር የድርሻውን ኃላፊነት እንደሚወጣ የተናገሩት ከንቲባው፣በአደጋው በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም፤የአደጋውን መንስኤም ፖሊስ እያጣራ መሆኑ ተነግሯል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply