የእስራኤል መከላከያ ኃይል የደህንነት ኃላፊ ከስራቸዉ ለቀቁ

በሀገሪቱ መከላከያ ኃይል የደህንነት ኃላፊ ሜጀር ጀነራል አሃሮን ሃሊቫ በገዛ ፍቃዳቸዉ ስልጣናቸዉን እንደለቀቁ ተሰምቷል፡፡

ሃሊቫ ስልጣናቸዉን የለቀኩት የወታደራዊ ኃይሉ እንዲዘምንና እንዲለወጥ በማስብ ነዉ ብለዋል፡፡

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣዉ መግለጫ ኃላፊዉ በቅረቡ እንደሚተኩ አስታዉቋል፡፡

ይሁን እንጅ የደህንነት ኃላፊዉ ሜጀር ጀነራል አሃሮን ሃሊቫ ከስልጣን ቢለቁም ከሃማስ ጥቃት ጋር ተያይዞ ተጠያቂ መሆናቸዉ አይቀርም እየተባለ ነዉ፡፡

ጀነራሉ በእስራኤል ጦር ዉስጥ ለ38 አመታት በተለያዩ ቦታዎች ያገለገሉ ናቸዉ ፡፡

አባቱ መረቀ

ሚያዝያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply