የእስራኤል ሚኒስትሮች አገራቸው የተኩስ አቁም ለማድረግ ከተስማማች ጥምር መንግሥቱን እናፈርሳለን ሲሉ ዛቱ፡፡ሁለት ቀኝ ዘመም የእስራኤል ሚኒስትሮች አገራቸው የተኩስ አቁም ለማድረግ ከተስማማች…

የእስራኤል ሚኒስትሮች አገራቸው የተኩስ አቁም ለማድረግ ከተስማማች ጥምር መንግሥቱን እናፈርሳለን ሲሉ ዛቱ፡፡

ሁለት ቀኝ ዘመም የእስራኤል ሚኒስትሮች አገራቸው የተኩስ አቁም ለማድረግ ከተስማማች ጥምር መንግሥቱን አፍርሰን ስልጣን እንለቃለን ሲሉ መዛታቸው ነው የተገለጸው።

ሁለቱ ሚኒስትሮች ይህን ያሉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በጋዛ ያለውን ጦርነት ለማስቆም አማራጭ ያሉትን መፍትሄ ማቅረባቸውን ተከትሎ ነው።

የፋይናንስ ሚኒስትር ቤዛሌል ስሞትሪች እና የብሔራዊ ደኅንነት ሚኒስትር አታማር ቤን-ጋቪር ሐማስ ሙሉ በሙሉ ሳይወገድ እስራኤል ወታደራዊ እርምጃዋን የሚያስቆም የተኩስ አቁም ስምምነት መድረስ የለባትም ብለዋል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች ይህን ይበሉ እንጂ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ያኢር ላፒድ የኔታኒያሁ መንግሥት የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ቢወስን ለመንግሥት ድጋፍ እሰጣለሁ ብለዋል።(ቢቢሲ)

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply