የእስራኤል ደህንነት ተቋም እና ሞሳድ ሃላፊዎች ወደ ግብጽ ሊያቀኑ ነዉ፡፡ሃላፊዎቹ በእስረኞች ጉዳይ ላይ ለመነጋገር ወደ ግብጽ ሊያቀኑ መሆኑ ተገልጿል፡፡የደህንነት ተቋሙ ሃላፊዎች ከሃማስ ጋር…

የእስራኤል ደህንነት ተቋም እና ሞሳድ ሃላፊዎች ወደ ግብጽ ሊያቀኑ ነዉ፡፡

ሃላፊዎቹ በእስረኞች ጉዳይ ላይ ለመነጋገር ወደ ግብጽ ሊያቀኑ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የደህንነት ተቋሙ ሃላፊዎች ከሃማስ ጋር ስለሚደረገዉ የእስረኛ ልዉዉጥ አዲስ ለዉጥ ካለ ለመምከር ወደ ግብጽ ካይሮ እንደሚያቀኑ የእስራኤል ጋዜጦች እያስነበቡ ይገኛል፡፡

ጀሩሳሌም ፖስት እንዳስነበበዉ የሞሳድ ዳይሬክተር ዴቪድ ባርኒያ እና የደህንነት ተቋሙ ሃላፊ ሮነን ባር በጋዛ ተይዘዉ ስላሉ የጦር እስረኞች ለመነጋገር በሚቀጥለዉ ሳምንት ወደ ግብጽ ካይሮ ያመራሉ፡፡

በንግግሩ ላይ የሲአይኤዉ ዋና ሃላፊ ዊሊያም በርንስ፣ የግብጽ የደህንነት ቢሮ ዳይሬክተር አባስ ካሜል እና የኳታሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ቢን አብዱልራህማን ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡

የአሜሪካዉ የደህንነት ቢሮ ሲአይኤ ሃላፊ ዊሊያም በርንስ በመጪዎቹ ቀናት ወደ ግብጽ ካይሮ እንደሚጓዙም ተገልጿል፡፡

በእስከዳር ግርማ
የካቲት 04 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply