የእስራኤል ጦር 13 ታጋቾችን ከቀይ መስቀል ተረከበ፡፡የእስራኤል ጦር ሐማስ የለቀቃቸውን 13 ታጋቾች መረከቡ ተዘገበ።የፈረንሳይ ዜና ወኪል የሆነው አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የእስራኤል የደኅንነት…

የእስራኤል ጦር 13 ታጋቾችን ከቀይ መስቀል ተረከበ፡፡

የእስራኤል ጦር ሐማስ የለቀቃቸውን 13 ታጋቾች መረከቡ ተዘገበ።
የፈረንሳይ ዜና ወኪል የሆነው አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የእስራኤል የደኅንነት ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ጦሩ ታግተው የነበሩ ሰዎችን ከቀይ መስቀል ተረክቧል።

ቀደም ሲሉ ከሐማስ እገታ ነጻ ይወጣሉ የተባሉት 13 ታጋቾች ለቀይ መስቀል ተላልፈው መሰጠታቸው ተገልጾ ነበር።

ታጋቾቹ በጋዛ እና ግብፅ መካከል በሚገኘው የራፋህ የድንበር በር አልፈው ወደ ግብፅ ተሻግረው ነበር።

ይህን ሂደት ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ከከፍተኛ የአገሪቱ ጦር መኮንኖች ጋር በመሆን በቅርበት ሲከታተሉት ቆይተዋል።

በእስራኤል እና በሐማስ መካከል በተደረሰው ስምምነት መሠረት ዛሬ ጠዋት የጀመረው እና ለቀናት የሚቆየው ጦርነት ጋብ የማድረግ አካል የሆነው የታጋቾች መለቀቅ በቀጣይ ቀናትም እንደሚቀጥል ይጠበቃል።

በያይኔ አበባ ሻምበል

Source: Link to the Post

Leave a Reply