የእስራኤል ፖሊሶች ከፍልስጤማውያን ጋር ግጭት መፍጠራቸው ተሰማ።
በተከበረው የእስራኤል የነጻነት ቀን፣ ፖሊስ የፍልስጤም ተቃዋሚዎች ላይ እርምጃ በመውሰዱ በእየሩሳሌም አል-አቅሳ መስጊድ ሁከት መቀስቀሱን አር ቲ ኒውስ
ዘግቧል ።
በክብረ በዓሉ እለት እስራኤል ፍልስጤማዊያን በሚገኙበት ቀጠና የእስራኤል ሰንደቅ አላማ እንዲውለበለብ የሚያዙ መመሪያዎቹን አውጥታ እንደነበር ተገልጿል ።
ነገር ግን ፍልስጤማውያን ለወጣው መመሪያ ተገዢ ከመሆን ይልቅ ግድየለሽነትን እያሳዩ ነው በሚል በእስራኤል ሃይሎች እርምጃ ተወስዷል ተብሏል ።
እስራኤልም አመፁን ያስጀመሩት ፍልስጤማዊያን መሆናቸውን በመግለፅ ፤በእሳት እየተጫወቱ እና ቀጣናውን ወደ ከፋ ደረጃ እንዲሄድ እያደረጉ ነው ስትል አስጠንቅቃለች ።
የአይን ምስክሮች ደግሞ አመፁን ያስጀመሩት ፍልስጤማውያን ናቸው የሚለውን ሃሳብ ከእውነት የራቀ ነው ብለዋል ።
በተወሰደው እርምጃ የሞቱ አልያም ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ይኑሩ አይኑሩ መረጃው መረጃው ያለው ነገር የለም።
በመሳይ ገ/ መድህን
ሚያዝያ 28 ቀን 2014
Source: Link to the Post