You are currently viewing የእነ መስከረም አበራ ችሎት! ጋዜጠኛ መስከረም አበራ “የታሰርኩት መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ የሚተገብረውን ፖሊሲ በመተቸቴ ነው” አለች  ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣…

የእነ መስከረም አበራ ችሎት! ጋዜጠኛ መስከረም አበራ “የታሰርኩት መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ የሚተገብረውን ፖሊሲ በመተቸቴ ነው” አለች ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣…

የእነ መስከረም አበራ ችሎት! ጋዜጠኛ መስከረም አበራ “የታሰርኩት መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ የሚተገብረውን ፖሊሲ በመተቸቴ ነው” አለች ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ዛሬ ግንቦት 10/2015 ዓ/ም ጋዜጠኛ መስከረም አበራን ጨምሮ ስድስት ተከሳሾች የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ጊዜ ቀጠሮ ምድብ ችሎት ቀርበዋል። ፖሊስ በዛሬው ቀጠሮ እነ ጋዜጠኛ መስከረም አበራ ላይ የሰነድ ፣ የቴክኒካልና ፎረንሲክ ማስረጃዎችን እንዲሁም የሰው ምስክሮችን በከፊል አሰባስቤያለሁ የተቀሩትን ለማጠናቀቅ የ14 ቀን ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ጠይቋል። “ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን በሁከትና ብጥብጥ ወንጀል ጠርጥሬያቸዋለሁ ባለበት ወቅት ያሰባሰባቸውን ማስረጃዎች ነው አሁን በሽብር ወንጀል በከሰሰበት ወቅት እያቀረበ ያለው” ሲሉ ጠበቆቹ ተከራክረዋል። በተጨማሪም መርማሪ ፖሊስ ወንጀሉ የተፈፀመው በአመራር ደረጃ ነው ማለቱን የተቃወሙት ጠበቆቹ ከተጠርጣሪዎቹ ውስጥ አመራር የሆነ ሰው እንደሌለም ለችሎቱ አስረድተዋል። በተጨማሪም ጠበቆቹ እነ መስከረም በዋስ ቢወጡ መረጃ የማጥፋትም ሆነ ፣ ከአገር የመውጣት እድል ስለሌላቸው ዋስትናቸው እንዲጠበቅ ችሎቱን ጠይቀዋል። በችሎቱ የተናገረችው መስከረም አበራ በበኩሏ “የታሰርኩት በፖለቲካ ምክንያት ነው፣ መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፅመውን ፖሊሲ በሚዲያ በመተቸቴ ነው የታሰርኩት፣ ሌላ ወንጀል አልሰራሁም” ብላለች። “የአማራ ህዝብ መብቱን ለማስከበር ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የፀጥታ አካላት ጥይት በመተኮሳቸው ለተነሳው አመፅ እኔ ተጠያቂ አይደለሁም ” ስትልም አክላለች። የግራ ቀኙን ያደመጠው ችሎቱም በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ አርብ ግንቦት 11/2015 ዓ/ም ቀጠሮ ሰጥቷል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply