You are currently viewing #የእነ ረዳት ፕ/ር ሲሳይ  የርሃብ አድማ ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸውን ጨምሮ 40 የሚሆኑ እስረኞች የርሃብ አድማ መጀመራቸው ተነገረ በአማራ ክልል ከልዩ ሃይል መፍረስና ፋኖን ትጥቅ ከማ…

#የእነ ረዳት ፕ/ር ሲሳይ የርሃብ አድማ ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸውን ጨምሮ 40 የሚሆኑ እስረኞች የርሃብ አድማ መጀመራቸው ተነገረ በአማራ ክልል ከልዩ ሃይል መፍረስና ፋኖን ትጥቅ ከማ…

#የእነ ረዳት ፕ/ር ሲሳይ የርሃብ አድማ ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸውን ጨምሮ 40 የሚሆኑ እስረኞች የርሃብ አድማ መጀመራቸው ተነገረ በአማራ ክልል ከልዩ ሃይል መፍረስና ፋኖን ትጥቅ ከማስፈታት ጋር ተያይዞ ለእስር የተዳረጉ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች የርሃብ አድማ መጀመራቸው ተነግሯል።… እስረኞቹ የርሃብ አድማውን ማድረግ የጀመሩት በአማራ ክልል የሚካሄደውን እስርና አፈና በመቃወም መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ለሮሃ ቲቪ ተናግረዋል። ከዛሬ ሰኞ ግንቦት ሰባት ጀምሮ እስከ ረቡእ ግንቦት 9 የሚቀጥል መሆኑንም ነግረውናል። በዚህም ” ሽብር፣ ሁከትና ብጥብጥ ፈጥራችኃል እየተባለ የአማራ ሙሁራንን፣ ጋዜጠኞችንና ወጣቶችን እንዲሁም የቀን ሠራተኞችን ማሰር ይቁም” በሚል እነ ረ/ፕ ሲሳይን ጨምሮ 40 የሚሆኑ ታስረው የሚገኙ የአማራ ሙሁራንና ሌሎች እስረኞች ናቸው የርሃብ አድማውን የጀመሩት። አድማውን አስመልክቶ ስለጉዳዩ ያውቁ እንደሆን ያናገርናቸው የእስረኞቹ ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝም ጉዳዩን ከእስረኞቹ ቤተሰቦች ከሰሙ በኋላ ወደ እስር ቤት በማምራት አድማ መጀመራቸውን እንዳረጋገጡ ነግረውናል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply