የእነ አቶ እስክንድር ነጋ ችሎት ሆንተብሎ በጥቃቅን ነገሮች እንዲዘገይ መደረጉ በምርጫው እንዳይሳተፉ በማድረግ የፖለቲካ ፍላጎትን ከማስፈፀም ጋር ይያያዛል ብሎ እንደሚያምን ጠበቃ ሄኖክ አክሊ…

የእነ አቶ እስክንድር ነጋ ችሎት ሆንተብሎ በጥቃቅን ነገሮች እንዲዘገይ መደረጉ በምርጫው እንዳይሳተፉ በማድረግ የፖለቲካ ፍላጎትን ከማስፈፀም ጋር ይያያዛል ብሎ እንደሚያምን ጠበቃ ሄኖክ አክሊ…

የእነ አቶ እስክንድር ነጋ ችሎት ሆንተብሎ በጥቃቅን ነገሮች እንዲዘገይ መደረጉ በምርጫው እንዳይሳተፉ በማድረግ የፖለቲካ ፍላጎትን ከማስፈፀም ጋር ይያያዛል ብሎ እንደሚያምን ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ተናገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 6 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከአማራ ሚዲያ ማዕከል ጋር ስለእነ እስክንድር ነጋ ችሎት ጉዳይ ቆይታ ያደረገው ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ሂደቱ በአቃቢ ህግ ያልተገባ አካሄድና በፍ/ቤቶችም ተባባሪነት በጥቃቅን ምክንያቶች እንዲዘገይ እየተደረገ ነው ብሏል። የባልደራስ መኢአድ ፕሬዝዳንት የአቶ እስክንድር ነጋ እና የባልደራስ አመራሮች ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩምና የእነ አስካለ ደምሌ ጉዳይ ምንም እንኳ ከታሰሩ 8 ወራት ቢሆንም ሂደቱ ዛሬም ከምስክር አሰማም ውዝግብ አለማለፉን ነው ጠበቃ ሄኖክ የተናገረው። እነ አቶ እስክንድር ነጋ አለም አቀፍ ተሞክሮን የያዘ ጥናት በማቅረብ ምስክሮች በግልፅ ችሎት እንዲሰሙ የተከራከሩበትና ብዙ ጊዜ የወሰደው ከመጋረጃ ጀርባ ይሁን የሚለው የአቃቢ ህግ አቤቱታ ጉዳይ ዛሬም እልባት አላገኘም። አሁንም አቃቢ ህግ እስከ ጠቅላይ ፍ/ቤት እና ሰበር ሰሚ ችሎት በማቅናት ምስክሮች ከመጋረጃ በስተጀርባ እንዲመሰክሩለት ባቀረበው አቤቱታ መሰረት ተከሳሾች የካቲት 5 ቀን ከማ/ቤት ሳይቀርቡ ጉዳዩ ታይቶ ለፊታችን የካቲት 8 ቀን 2013 ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል። በጉዳዩ ላይ ከጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ጋር ቆይታ አድርገናል፤ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply