
የእናት ፓርቲ፣ መኢአድ እና ኢህአፓ ትብብር አዲስ ከተቀላቀላቀሏቸው ሁለት ፓርቲዎች ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ የፊታችን ረቡዕ ሃምሌ 5 ቀን ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል፤ የመገናኛ ብዙሃን በስፍራው እና በሰዓቱ ተገኝተው የዘገባ ሽፋን እንዲሰጡ ጠይቀዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 3/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ጉዳዩ፦ ጋዜጣዊ መግለጫ:_ የእናት ፓርቲ፣ መኢአድ እና ኢህአፓ ትብብር ረቡዕ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓም ከጠዋቱ 4፡30 ስድስት ኪሎ በሚገኘው የእናት ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት አዲስ ትብብሩን ከተቀላቀሉ ፓርቲዎች ጋር በመሆን በአገራችን ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል። በዚሁ መሠረት ተቋማችሁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በቦታው በመገኘት የመገናኛ ብዙኅን ሽፋን እንድትሰጡ በአክብሮት እንጋብዛለን። እግዚአብሔር አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አድራሻ:_ በያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት በኩል ወረድ ብሎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ያኔት ኮሌጅ የሚገኙበት ሕንጻ ላይ 3ኛ ፎቅ
Source: Link to the Post