የእናት ፓርቲ በደቡብ ጎንደር ዞን ታች ጋይንት ወረዳ ሰብሳቢ ሰለሞን ዲበኩሉ ታሰሩ

ማክሰኞ ግንቦት 20 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በደቡብ ጎንደር ዞን የታች ጋይንት ወረዳ የእናት ፓርቲ ሰብሳቢ የሆኑት ሰለሞን ዲበኩሉ ተፈራ ግንቦት 16 ቀን 2016 በጸጥታ ኃይሎች ተወስደው መታሰራቸው እናት ፓርቲ ዛሬ አስታወቀ።

አዲስ ማለዳ ከፓርቲው ያገኘችው መረጃ እንደሚያመላክተው፤ በአሁኑ ሰአት በላይ ጋይንት ማረሚያ ቤት እንደሚገኙ እንዲሁም ከእርሳቸው ጋር አብረው አምስት የአካባቢው ወጣቶችም ታስረዋል።

ሰለሞን ዲበኩሉ የታሰሩበት ምክንያት እስካሁን ድረስ ያልተነገራቸው ሲሆን ክስም እንዳልተመሰረተባቸው የገለጸው ፓርቲው፤ “የፓርቲያችን አባላት አፈና እና እስር የፖለቲካችን ስብራት አንድ ማሳያ መሆኑን እየገለጽን፤ ትግላችን ሰላማዊ በመሆኑ መንግሥት አባላቶቻችንን እያሳደደ ማሰሩን እንዲያቆም” ሲል አሳስቧል። በፍርቱና ወልደአብ

Source: Link to the Post

Leave a Reply