You are currently viewing የእናት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አቶ ሀብታሙ ይታየው ንጉሴ በፍርድ ቤት በነጻ ተሰናበተዋል።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም          አዲስ አበባ ሸዋ  የእና…

የእናት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አቶ ሀብታሙ ይታየው ንጉሴ በፍርድ ቤት በነጻ ተሰናበተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የእና…

የእናት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አቶ ሀብታሙ ይታየው ንጉሴ በፍርድ ቤት በነጻ ተሰናበተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የእናት ፓርቲ የላዕላይ ምክር ቤት አባል እና የመተከል ምርጫ ክልል 1 የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዕጩ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ይታየው ንጉሴ በ23/01/2015 ዓ.ም ጠዋት እንፈልግሃለን ተብለው በፖሊሶች ከቤታቸው ከተወሰዱ በኋላ በተለያየ እስር ቤት ውስጥ ለሳምንት ሲንገላቱ የቆዩ ቢሆንም በዛሬው እለት ፍርድ ቤት በነጻ እንዳሰናበታቸው ተገልጧል። አቶ ሀብታሙ ይታየው በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ ለሚመለከታቸው አካላት ማለትም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በደብዳቤ በማሳወቀ እና ጠበቃ በማቆም ጉዳዩንም በቅርበት በሚከታተልበት ሰዓት ተቋማዊ ሓላፊነታችሁን ለመውጣት ቅን ትብብር ላደረጋችሁ ሁሉ እናት ፓርቲ ከፍተኛ ምሥጋና አቅርቧል። በተጨማሪም የአቶ ሀብታሙ እስር አሳስቧችሁ በአካልም በመገኘት ስትጠይቁ ለነበራችሁ፣ ከርቀት ሆናችሁም ስትጨነቁ ለነበረ የፓርቲው አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎችና አጋሮች ሁሉ ልባዊ ምሥጋና ይድረሳችሁ ብሏል እናት ፓርቲ። በልዩ ምሥጋና፣ በተለይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሓላፊ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ለፈጣንና ቅን ምላሻቸው፣ ጠበቃ አዲሱ ጌታቸው እና ጠበቃ ጎሽራድ ፀጋው ላደረጋችሁት ሙያዊ እገዛም ፓርቲው ምሥጋና አቅርቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply