
የእናት ፓርቲ የላዕላይ ምክር ቤት አባላት የምክር ቤቱን አፈ ጉባኤ እና ምክትል አፈ ጉባኤ መርጠዋል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 13/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ የእናት ፓርቲ የላዕላይ ምክር ቤት አባላት ግንቦት 12/2015 ዓ.ም ባከናወኑት ስብሰባ የምክር ቤቱን አፈ ጉባኤና ምክትል አፈ ጉባኤ መርጠዋል። የምክር ቤት አባላቱ ረዳት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ፀሐይን፣ መምህር ዶ/ር ናሁሰናይ አባተን፣ ኢ/ር ማትያስ በትረን እና አቶ ያየህ አስማረን በእጩነተ አቅርበው በሰጡት ድምጽ አቶ ያየህ አስማረን በአፈ ጉባኤነት እንዲሁም ረ/ ኘሮፌሰር ብርሃኑ ፀሐይን በምክትል አፈ ጉባኤነት መርጠዋል። እናት ፓርቲ እንዳጋራው።
Source: Link to the Post