You are currently viewing የእናት ፓርቲ ፕሬዝደንት እና የፓርቲው ዋና ጸሀፊ ከፈረንሳይ እና ከእንግሊዝ ኤምባሲ ኃላፊዎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ምክክር ማድረጋቸው ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     የካቲ…

የእናት ፓርቲ ፕሬዝደንት እና የፓርቲው ዋና ጸሀፊ ከፈረንሳይ እና ከእንግሊዝ ኤምባሲ ኃላፊዎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ምክክር ማድረጋቸው ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲ…

የእናት ፓርቲ ፕሬዝደንት እና የፓርቲው ዋና ጸሀፊ ከፈረንሳይ እና ከእንግሊዝ ኤምባሲ ኃላፊዎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ምክክር ማድረጋቸው ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 2 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የእናት ፓርቲ ዋና ጸሀፊ አቶ ጌትነት ወርቁ ጥር 30 እና የካቲት 1/2015 ከፓርቲው ፕሬዝደንት ከዶ/ር ሰይፈ ስላሴ ጋር በመሆን ከፈረንሳይ እና እንግሊዝ ኤምባሲ ኃላፊዎች ጋር ግሩም እና ወዳጃዊ ውይይት አድርገናል ሲሉ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው አጋርተዋል። አቶ ጌትነት ወርቁ እንደገለጹት ለኤምባሲ ኃላፊዎች አጽንኦት ሰጥተው ካሳሰቡት መካከል:_ 1) እየሆነ ያለውን ነገር የየሀገራቸው መንግሥታት በውል እንዲረዱት፣ 2) ልታደርጉ የምትችሉት ነገር ካለ የጸጸት ደብዳቤ ከምትልኩ አኹኑኑ አድርጉ፣ 3) የዐቢይ መንግሥት የሚያደርገውን አይደለም የሚለውን እንኳን የማያውቅ እየሆነ ነው፣ 4) ቤተክርስቲያንን በመክፈል ሀገርን ለማፍርስ እየሠራ ነው የሚል ከፍተኛ ጥርጣሬ አለን፣ 5) በተለይ የሃይማኖት ጉዳይ በመሆኑና እንደባህልና ጽድቅ “ሰማዕትነት እንዳያልፋችሁ” እያለ ወደሞት የሚተም ሕዝብ ነው ይህን ደግሞ መንግሥት ያወቀ አይመስልም፣ እጅግ ሥጋት ገብቶናል፣ 6) እንዲህ ከቀጠለ እናንተ የምትጓጉለት ሀገራዊ መግባባት አይደለም ምሥራቅ አፍሪካን የሚንጥ አለመረጋጋት ሊከሰት ይችላል፣…ብለን ወትውተናል ብለዋል። ውትወታችንን በደምንብ አድምጠውናል ያሉት አቶ ጌትነት ጥረታችንን እንቀጥላለን፣ሁኔታውን በዐይን ጥቅሻ ላመቻቹት ወጣቶቹ የፖለቲካ ክፍል ሓላፊዎች ምስጋና እናቀርባለን ብለዋል። በተያያዘም ቤተ ክርስቲያን እንደጽኑ፣ ሕጋዊ፣ ጥንታዊ ተቋም የdiplomatic ማኅበረሰቡን በአስቸኳይ ቢቻል ከሰልፉ በፊት ጠርታ ስለሁኔታው በደንብ ገለጻ ማድረግ አለባት ሲሉም ምክረ ሀሳብ አስቀምጠዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply