የእናቶችና ጨቅላ ህፃናትን ሞት

https://gdb.voanews.com/03370000-0aff-0242-7ceb-08dacd8e2a98_tv_w800_h450.jpg

በኢትዮጵያ በተለይ በገጠርና ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ነፍሰ ጡር እናቶች ተገቢውን ሕክምና ባለማግኘታቸው ምክኒያት እናቶችና ጨቅላ ሕፃናት እንደሚሞቱ የጤና ባለሞያዎች ይናገራሉ። 

በምስራቅ ወለጋ ዴዴሳ ቀበሌ ነዋሪዋ ወ/ሮ ሌሊሴ ጃዋር ምስራቅ ከሦስት ቀናት በፊት ለወሊድ ሆስፒታል ቢገቡም ልጃቸውን ግን መታቀፍ እንዳልቻሉ ይናገራሉ።

ግጭት ተከስቶበት በነበረው ራያ ቆቦ ከተማ ነዋሪ እንደሆኑ የሚናገሩት ወ/ሮ ጎዳዳ ሞላ በበኩላቸው በአካባቢው በነበረው ጦርነት ይበልጥ ተጎጂ የነበሩት እናቶችና ህፃናት እንደነበሩ ይናገራሉ። 

በአምቦ አጠቃላይ ሆስፒታል የፅንስና ማኅፀን ስፔሻሊስት ዶ/ር ኃይሌገመቹ በበኩላቸው ነፍሰ ጡር እናቶችተገቢውን ክትትል የማያገኙ በመሆኑ ለጉዳት እንደሚዳረጉ ገልፀዋል። 

በሌላ በኩል በኢትዮጵያ በዓመት 14 ሺህ የሚሆኑ እናቶች በወሊድ ምክንያት ህይወታቸውን እንደሚያጡ ጤና ሚኒስቴር ገጿል። ከ87 ሺህ በላይጨቅላ ህፃናትም በወሊድ ላይ በሚከሰት የጤና እክል ህይወታቸው እንደሚያልፍ የጤና አስታውቋል።

በጤና ሚኒስቴር የእናቶች እና ህፃናት ጤና ዳይሬክተር ዶክተር መሰረት ዘላለም በኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወሊድ ምክንያት የሚሞቱ እናቶች እና ጨቅላ ህፃናትን ለመታደግ ሚኒስተሩ በተቀናጀ ሁኔታ ሥራ ጀምሯል ብለዋል። 

/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ይከታተሉ/

 

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply