የእናቶች፣ ወጣቶችና የህጻናት ጤና አቅርቦት እንዳይጓደል በአንድነት መስራት ይገባል – ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

የእናቶች፣ ወጣቶችና የህጻናት ጤና አቅርቦት እንዳይጓደል በአንድነት መስራት ይገባል – ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የእናቶች፣ የወጣቶችና የህጻናት ጤና አቅርቦት እንዳይጓደል ሁሉም በአንድነት መስራት እንዳለበት ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንቷ የእናቶች፣ የጨቅላ ህጻናት እና የልጆች ጤና አጋርነት በተባለ ድርጅት በተዘጋጀ ዉይይት ላይ ተሳትፈዋል፡፡

በዚህ ወቅትም ለእናቶች፣ ወጣቶችና ህጻናት ጤና እንዳይጓደል ሁሉም መስራት ይገባዋል ብለዋል፡፡

ውይይቱ በቀድሞዋ የኒውዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር አወያይነት የመንግስት፣ የሲቪክ ማህበራት እንዲሁም የወጣቶች ተወካዮች የተሳተፉበት እንደነበር ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

The post የእናቶች፣ ወጣቶችና የህጻናት ጤና አቅርቦት እንዳይጓደል በአንድነት መስራት ይገባል – ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply