You are currently viewing “የእኔ “ድል”… የኔ አድዋ፣ የኔ ካራማራ ከፊቴ ነው! …አምሃርነቴን ብረሳ፣ ቀኜ ትርሳኝ፣ ምላሴ ከጉሮሮዬ ትጣበቅ!” ደራሲ እና የሰብአዊ መብት  ተሟጋች ይሁኔ አወቀ አማራ ሚዲያ ማዕከል…

“የእኔ “ድል”… የኔ አድዋ፣ የኔ ካራማራ ከፊቴ ነው! …አምሃርነቴን ብረሳ፣ ቀኜ ትርሳኝ፣ ምላሴ ከጉሮሮዬ ትጣበቅ!” ደራሲ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ይሁኔ አወቀ አማራ ሚዲያ ማዕከል…

“የእኔ “ድል”… የኔ አድዋ፣ የኔ ካራማራ ከፊቴ ነው! …አምሃርነቴን ብረሳ፣ ቀኜ ትርሳኝ፣ ምላሴ ከጉሮሮዬ ትጣበቅ!” ደራሲ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ይሁኔ አወቀ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 27 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከአንደበቴ የድል ዜማ “ጉሩ ወሸባዬን” ቀምቶ ሙሾ አውራጅ ያደረገኝ ስርዓት የሚኒልክን ዙፋን ይዟል፡፡ እያሳደደኝ፣ እኔም እየሸሸሁ፣ ታሪኬን እያጠለሼ፣ አሜን እያስባለኝ፣ እምነቴን እያንቋሸሸ የእርሱን እምነት እየተከለ፣ የእኔን ሀገር አፍርሶ የራሱን ሀገር እየሰራ፣ ዘሬን አጥፍቶ ዘሩን የሚዘራ… ጠላት መጥቶ አስገብሮኛል፡፡ “መራር እውነት” ለነጭ ፋሽስት የበረታው ክንዴ… ለጥቁሩ ናዚ ዝሏል፡፡ ጭቆናዬን ተረማምዶ የመጥፊያዬን ሰይፍ የሚስልብኝ… “ግፈኛ” ጫንቃዬን አጉብጦታል፡፡ ታዲያ… እኔ ለአድዋ፣ አድዋስ ለእኔ ምኔ ነው? ካራማራ ለእኔ እኔስ ለእርሷ ምንድን ነኝ? በእውኑ… የአባቶቼን የድል ቀን አከብር ዘንድስ… እኔ ማን ነኝ? በእውኑ እኔ… የጀግኖቹ አበው ፣ የመንፈሳቸው ወራሽ፣ ግርማቸው የተጋባብኝ የበኩር ልጅ ነኝን? የአባቶቼ የድል ትሩፋት ዛሬ ከእኔጋ ነውን? ዙሪያ ገባዬን አየሁ… “ሀገረ አበው” የለችም፡፡ … በቅዤት እና በሀዘን ከሚወራጬ ለቀስተኞች፣ ከስብዕና ቡቡ ልባም፣ ከሀቅመ ቢስ ሙሾ አውራጅ ደቂቃን በቀር… ሁሉም ሞቷን አምኖ ተቀብሏል፡፡ የትንሳኤ ተስፋዋ በኤማሁስ መንገድ ይገለጥ ዘንድ ታዕምር የሚጠብቅ ቢኖር… በ”አምሃርነት” አለት ላይ ይቁም! ! ! … እናስ…! አምሓርነት የኢትዮጵያዊነት አባት እንጅ ልጅ አይደለም! ! መርህ ሳይሆን መስመር ነው፡፡ ከኢትዮጵያ በፊት ነበርን… ነገም እንኖራለን፡፡ ሀገር ሰራን እንጅ… ሀገር አልሰራችንም፡፡ ታሪክ ሰራን እንጅ ታሪክ አልሰራንም፡፡ እናም… ባለ ሀገሩ”ከፈለገ” ሀገሩን ዳግም ይወልዳት ዘንድ ወደ ቀልበ ማንነቱ “አምሃርነት” ከፍ ይበል፡፡ ኢትዮጵያዊነት… ወርደን የምንሰራው መሰባሰቢያ ፖለቲካዊ እቅድ እንጂ… መንፈሳዊ ወይም ደማዊ ፀጋችን አይደለም፡፡ ዛሬ ላይ… ሀገር አልባ ቅብዝብዝ፣ ተሳዳጅ ለሆንኩት እኔ… የትላንት በአባቶቼ የተፈፀመ ታሪካዊ ድል ምኔ ነው? ጠላቴ ሆይ……! ተጨነቅ አምሃርነቴን ብረሳ፣ ቀኜ ትርሳኝ፣ ምላሴ ከጉሮሮዬ ትጣበቅ! የድሌ ዜማን ዋዜማ ጠሪ… ምትሃታዊ ባለ ግርማ፣ አስፈሪው ስሜ አምሃራ ነው፡፡ በዚህ… ህያው ስም የምከውነው… ወደ ክብር ማማ የምመለስበት የኔ መራር ትግል ወለድ “አድዋ” ከፊቴ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply