የእንሳሮ ፋኖዎች ልብ የሚያሞቅ ጀብዱ ============ በ18/7/2016 ዓም በሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ በልበሊት ቀጠና ላይ የእራስ አበበ አረጋይ ብርጌድ 2ኛ ልጅ ስዩም ሻለቃ…

የእንሳሮ ፋኖዎች ልብ የሚያሞቅ ጀብዱ ============ በ18/7/2016 ዓም በሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ በልበሊት ቀጠና ላይ የእራስ አበበ አረጋይ ብርጌድ 2ኛ ልጅ ስዩም ሻለቃ የጠላትን ሀይል በመደምሰስ ታላቅ ጀብዱ ፈጸመ። የጠላት የፋሽስቱ አብይ አህመድ ሰራዊት ከለሚ ተነስቶ ወደ መርሀቤቴ ወረዳ የጦር መሳሪያ ሲያጓጉዝ የፋኖ ሀይል የጠላትን እንቅስቃሴ በቅርብ እርቀት እየተከታተለ ለመራራ እርምጃ መዘጋጀት ጀመረ። በአቢይ አህመድ የሚመራዉ የኦነግ/ኦህዴድ ሀይልም በለሚ ቀጣና የሚንቀሳቀሰውን የልጅ ስዩም ሻለቃን ለመምታት ከለሚና ከመርሃቤቴ ሀይል አዉጣጥቶ በበርካታ ዲሽቃ፣እስናይፐር፣ብሬን የታገዘ ጥቃት ከፈተ። የጠላትን እንቅስቃሴ ልቅም አድርጎ ሲከታተል የነበረዉ የአበበ አረጋይ ብርጌድ 2ኛልጅ ስዩም ሻለቃም ለጠላት ሀይል የእግር እሳት በመሆን ከረፋዱ 5፡30 እስከ 7፡00 ሰአት መራራ ዉጊያ በማድረግ የኦነግ/ኦህዴድ ሀይልን ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ ደምሦታል። ከድምሰሳ ያመለጠዉ የተወሰነዉ የኦነግ/ኦህዴድ ሀይልም ሙትና ቁስለኛዉን እያንጠባጠበ ከአካባቢዉ ፈርጥጦ ሸሽቷል። ===== የመረጃ ምንጭ፥- የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ ዳዊት ክፍለ ጦር እራስ አበበ አረጋይ ብርጌድ 2ኛ ልጅ ስዩም ሻለቃ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ እዬብ እስጢፍኖስ

Source: Link to the Post

Leave a Reply