የእንቅልፍ ማጣት ችግር

እንደ ተመራማሪዎች ገለጻ እንቅልፍ ለአዕምሮ ንቃት እና ብርታት አስፈላጊ መሆኑ ይነገራል ።

አይናችንን ከድነን ለመተኛች መቸገር ወይም በአግባቡ አለመተኛት ደግሞ ከድካም በዘለለ የጤና እክሎች እንደሚያስከትል የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ሥራን በአግባቡ ለመስራት፣ ማህበራዊ ኑሮን ለማመጣጠን እንዲሁም ጤናማ ሆኖ ለመቆየት ጥሩ እንቅልፍ ወሳኝ መሆኑም ይታወቃል።

ስለ እንቅልፍ ማጣት ችግርም ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን የስነ-ልቦና ባለሙያ ከሆኑት ቴድሮስ ድልነሳው ጋር ጣቢያችን ቆይታ አድርጓል፡፡

የእንቅልፍ ማጣት ችግር ምንድን ነው ?

እንቅልፍ ተፈጥሯዊ የሆነ ሂደት ነው በቀን ውስጥ አንድ አራተኛ የሚሆነውን በእንቅልፍ ነው የምናሳንፈው ይላሉ ባለሙያው፡፡

ታድያ ሰዎች ባላቸው የእለት ተዕለት መስተጋብር አንዳንዴ ለመተኛት ምቹ የሚሆኑ ጊዜያቶች ይኖራሉ አንዳንዴ ደግሞ ሳንተኛ እና በቂ እንቅልፍ ሳናገኝ ልንነቃባቸው የምንችላቸው ሁኔታዎቸ አሉ፡፡

ከብዙ የአእምሮ ጤና መዛባት ጋርም የእንቅልፍ ማጣት እንደ ምልክት ሆኖ ሊመጣ ይችላል፡፡

መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው?

 • የውጥረት መጠን መጨመር
 • እየጠጡ ማምሸት
 • ስልክ እና ኮምፒውተር ላይ እረዥም ሰዓት ማሳለፍ
 • ሰው ሰራሽ የሆኑ ክስተቶች(ጦርነት ፣ግጭት)
 • ተፈጥሯዊ የሆኑ አደጋዎች( ጎርፍ ፣ረሀብ፣ድርቅ) ውስጥ የሚያልፉ ሰዎች አዕምሯቸው ላይ የሚፈጥረው ጠባሳ እንቅልፍ ሊያሳጣቸው እንደሚችል ባለሙያው ይናገራሉ፡፡

ምን ሊያስከትል ይችላል?

 • ቀን ላይ የሚኖረን ንቃት እና ትኩረት መቀነስ
 • ድካም ድካም ማለት
 • ከባድ የሆነ የአዕምሮ ጤና መታወክ
 • የሀይል መቀነስ
 • መበሳጨት
 • ከሰዎች ጋር ለመግባባት መቸገር
 • የሰውነት በሽታን የመከላከል አቅም መቀነስ
 • መቆጣት
 • የማድመጥ አቅማችን ማነስ
 • አዕምሯችን ላይ የሚፈጥረው እረዥም ግዜ የሚቆይ ተፅእኖ ደግሞ ለሌሎች አካላዊ ህመሞች ሊያጋልጠን እንደሚችል አንስተዋል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍ ምን ማድረግ ይመከራል?

 • የሚረብሸን ነገር ካለ የቅርብ ለምንለው ሰው ማማከር
 • የስነ ልቦና ባለሙያዎች ማማከር
 • ሙቅ ሻወር መውሰድ
 • የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ
 • ትኩስ ወተት መጠጣት
 • ለእንቅልፍ የሚሆን ሁኔታ ማመቻቸት(ሲተኙ ከ100 ጀምሮ ወደኋላ ቁጥር እየቆጠሩ መተኛት)
 • የቀን ልምዳችንን መጠበቅ( ተመሳሳይ ሰዓት መተኛት እና መንቃት) ይጠቀሱበታል፡፡

በመጨረሻም ከጤና ጣቢያ ጀምሮ ያሉ የጤና ባለሙያዎችን ፣የስነ አዕምሮ ሀኪሞችን ፣ የስነ ልቦና ባለሙያዎችን ማናገር እና የሚያሳስቡን ነገሮች ሲኖሩ መፃፍ እንደሚጠቅም ባለሙያው ተናግረዋል፡፡

በሐመረ ፍሬው

ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply