You are currently viewing የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻሊስት ሀኪሞች የዓይን ህክምና ክፍል ከፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል እና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ለ3 ቀናት የሚቆይ ነጻ የዓይን…

የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻሊስት ሀኪሞች የዓይን ህክምና ክፍል ከፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል እና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ለ3 ቀናት የሚቆይ ነጻ የዓይን…

የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻሊስት ሀኪሞች የዓይን ህክምና ክፍል ከፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል እና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ለ3 ቀናት የሚቆይ ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ሊያከናውኑ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 8/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ የአይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ለእንጅባራ እና አካባቢው ማህበረሰብ:_ የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻሊስት ሀኪሞች የዓይን ህክምና ክፍል ከፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል እና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ከሐምሌ 28 እስከ 30/2015 ዓ.ም ባሉት ቀናት ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ለማከናወን አቅዷል። በዚሁ መሰረት ሐምሌ 22 እና 23 በዳንግላ፣ በቻግኒ እና በቲሊሊ ጤና ጣቢያዎች የበሰለ ሞራ ግርዶሽ ልየታ ያከናውናል። በእንጅባራ እና አካባቢው ደግሞ ከሐምሌ 24 ጀምሮ በእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል ልየታ ያደርጋል። በእነዚህ ቀናት ከዓይን ሞራ ልየታ በተጨማሪ ከ40 ዓመት በላይ ለሆኑ እና ለሚያነቡ ሰዎች ነፃ የማንበቢያ መነጸሮችን በልኬታቸው መሰረት ይሰጣል። ስለሆነም የእንጅባራ እና አካባቢው ማህበረሰብ የእድሉ ተጠቃሚ ለመሆን በተጠቀሱት ቀናት በሚቀርባችሁ ጤና ጣቢያ በመሄድ አገልግሎቱን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። በተጨማሪም የእንጅባራ ዩኒቨርስቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአይን ህክምና ትምህርት ክፍል ባልደረባ የሆኑት ዶ/ር ሰለሞን ተከወ በ2015 ዓ.ም መሰል የአይን ህክምና ዘመቻዎችን በእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል ሲያደርጉ ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑን ጠቅሰዉ ማህበረሰቡ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አሳስበዋል። ሐምሌ 8/2015 ዓ. ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ

Source: Link to the Post

Leave a Reply