
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወደ መጠናቀቂያው ተቃርቧል። የሊጉ 36ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜ ተጀምረው እሑድ እና ሰኞ ቀጥለው ይከናወናሉ። ለሊጉ ዋንጫ እና ላለመውረድ ከሚደረገው ትንቅንቅ በተጨማሪ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዞ በማጠናቀቅ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ የሚደረገው ፉክክርም አጓጊ ሆኗል። የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን በየሳምንቱ እንደሚያደርገው የዚህን ሳምንት ጨዋታዎች ውጤት እንደሚከተለው ገምቷል።
Source: Link to the Post