You are currently viewing የእንጦጦ አንባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን የሆኑት እነ መምህር ዘመነ ጌቴ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው ለይደር ተቀጥረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   መጋቢት 11 ቀን…

የእንጦጦ አንባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን የሆኑት እነ መምህር ዘመነ ጌቴ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው ለይደር ተቀጥረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 11 ቀን…

የእንጦጦ አንባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን የሆኑት እነ መምህር ዘመነ ጌቴ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው ለይደር ተቀጥረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 11 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የእንጦጦ አንባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን የሆኑት እነ:_ 1.ዘመነ ጌቴ (መምህር እና የመኢአድ ከፍተኛ አመራር) 2.ምስጋው ጫኔ፣ 3.ዘላለም ልዑል፣ 4.ታያቸው አካለው፣ 5.ማቲያስ መለሰ፣ 6.የቆየ አሻግሬ እና 7.ሠይፈ ታረቀኝ መጋቢት 08/2015 ዓ/ም አራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድን ቤት ቀርበው እያንዳንቸው በ2 ሽህ ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተሰጥቶ ነበር። ለዋስትና የተጠየቀው ገንዘብ ከተያዘ በኋላ ይግባኝ ጠይቀናል በሚል በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን መጋቢት 11/2015 በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበው ነበር። ይግባኙ የቀረበለት ከፍተኛው ፍርድ ቤትም በጉዳዩ ላይ ብይን ለመስጠት በሚል ለመጋቢት 12/2015 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል። ምንጭ_ለገሰ ወልደሀና ከመኢአድ

Source: Link to the Post

Leave a Reply