You are currently viewing “የእኛ የፖለቲካ ጥያቄ ሳይሆን  “የመኖር እና ያለ መኖር ጥያቄ ነው። የህይወት ጥያቄ ነው።” ሲሉ በኢትዮ ጅቡቲ መስመር የሚሰሩ የከባድ መኪና ሹፌሮች ገለጹ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ሀ…

“የእኛ የፖለቲካ ጥያቄ ሳይሆን “የመኖር እና ያለ መኖር ጥያቄ ነው። የህይወት ጥያቄ ነው።” ሲሉ በኢትዮ ጅቡቲ መስመር የሚሰሩ የከባድ መኪና ሹፌሮች ገለጹ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀ…

“የእኛ የፖለቲካ ጥያቄ ሳይሆን “የመኖር እና ያለ መኖር ጥያቄ ነው። የህይወት ጥያቄ ነው።” ሲሉ በኢትዮ ጅቡቲ መስመር የሚሰሩ የከባድ መኪና ሹፌሮች ገለጹ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 16 ቀን 2014 ዓ.ም… አዲስ አበባ ሸዋ ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ በጻፉት ደብዳቤ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች መብትና ግዴታቸውን ጠንቅቀው እንደሚያውቁና እንደሚወጡም አስታውቀዋል። “እኛ የፖለቲካ ጥያቄ የለንም። አንዳንድ ግለሰቦች ጥያቄያችንን ከፖለቲካ ጋር ሲያያይዙት ይስተዋላሉ” ብለዋል። ይልቁንስ “የእኛ ጥያቄ የመኖር ያለመኖር ጥያቄ ነው። የህይወት ጥያቄ ነው።ተገደልን፣ተዘረፍን፣ተጎዳን አድኑን ደህንነታችንን ጠብቁልን የሚል ነው።” ሲሉ አስረድተዋል። ሾፌሮቹ ሲቀጥሉ ጥያቄያቸውን ያልተረዱ የመንግስት አካላት ከተሳሳተ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል። “በአፋር ክልል ከሀዋሽ ሰባት እስከ ዲቺኦቶ፣ በሱማሌ ክልል ከሽንሌ እስከ ደወሌ ዝርፌያና ግድያ አየተፈፀመብን ነው። እንዲሁም በጂቡቲ ጀንደር መሪ ሰብአዊ መብታችን ተገፎ ጉቦ ከመስጠት አልፎ እስከ መደብደብ እስከ መታሰር ጥሰቶች እየተፈፀሙብን ነው” ሲሉ አማረዋል። “እስካሁን ድረስ በደላችንን ሁሉ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ሪፖርት ብናደርግም ተፈፃሚ የሚያደርግልን አጥተናል” ብለዋል። “እኛም ለልጆቻችን፣ለቤተሰቦቻችን መኖር እንፈልጋለን።” ያሉት ሾፌሮቹ በፎቶው ላይ እንደሚታየው ይህ ውሉ ጥይት የሚተኮሰው ወደ እኛ ነው። በአፋርና ሱማሌ ክልል ደህንነታችን ይጠበቅልን ዘንድ በእርስዎ በኩል መመሪያ እንዲሰጥልን በአክብሮት እንጠይቃለን።” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በደብዳቤ ጠይቀዋል። ለዘገባው ሸገር ፕሬስን በምንጭነት ተጠቅመናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply