#የእግር መደንዘዝና የማቃጠል ስሜት የሚፈጠረው ከፍተኛ የሰውነት ክብደት ያላቸው ሰዎች ክብደታቸው በመገጣጠሚያዎቻቸው ላይ በሚፈጥረው ተደጋጋሚ ጫና ምክንያት የነርቭ ሥርዓታቸው ሲዛባና እግራቸ…

#የእግር መደንዘዝና የማቃጠል ስሜት የሚፈጠረው ከፍተኛ የሰውነት ክብደት ያላቸው ሰዎች ክብደታቸው በመገጣጠሚያዎቻቸው ላይ በሚፈጥረው ተደጋጋሚ ጫና ምክንያት የነርቭ ሥርዓታቸው ሲዛባና እግራቸው ጉዳት ሲደርስበት ነው።

#ይህን ያሉን በሃሌታ ፊዚዮቴራፒ ክልኒክ የፊዚዮቴራፒ ስፔሻሊስት የሆኑት አቶ ማይክለ ተክሉ ናቸው።

#በዚህ በሽታ ታጋላጭ የትኞቹ ሰዎች ናቸው?

እንዲህ ያለው ሁኔታ በስፋት የሚታየው ዕድሜያቸው በገፋ፣ ከመጠን ያለፈ የሰውነት ክብደት ባላቸውና ምንም ዓይነት የሰውነት እንቅስቃሴ በማያደርጉ ሰዎች ላይ ነው፡፡

#የእግር መደንዘዝ፣ማቃጠልና ማስነከስ መንስኤ

– በኩላሊቶቻችን ላይ በሚደርሱ የጤና ችግሮች ሳቢያ
– በአከርካሪያችን ላይ የሚያልፈው ነርቭ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ሲጐዳ ነው፡፡

#ለነርቭ ሥርዓታችን መዛባት በምክንያትነት ከሚጠቀሱ ችግሮች መካከል;- የደም ቧንቧ መታወክ፣ የዲስክ መንሸራተት (በአከርካሪያችን ንብርብር ላይ የሚገኘውና ዲስክ በመባል የሚጠራው የአካላችን ክፍል ትክክለኛ ቦታውን ለቆ ነርቫችንን ሲጫነው) እና በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰቱ አደጋዎች እንዲሁም ኢንፌክሽኖች ይገኙበታል፡፡

የእግሮቻችን ጤና ከደም ዝውውርና ከነርቭ ሥርዓት መታወክ እንዲሁም ኩላሊትንና ልብን ጨምሮ ከሌሎች የውስጥ ደዌ በሽታዎችና ከአደጋ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች ሊታወክና እንደ ልብ ከመንቀሳቀስ ሊያግደን ይችላል፡፡

#ህክምና ምንድነው ?

በባለሙያ የታገዘ የመዳኒትና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
የህክምና ዓይነቶች ከቀላል የነርቭ ህክምና እስከ ቀዶ ህክምና ድረስ የሚዘልቁ ህክምና ዘዴ አለ፡፡

#የእግር ህመም ከመከሰቱ በፊት እንዴት መከላከል ይቻላል ።

ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን መከተል፣የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣የሰውነት ክብደትን መቀነስ ፣ቀለል ያሉና ምቾት የሚሰጡ ጫማዎችን መጠቀም፣ የኩላሊት የጉበት፣ የልብና የደም ግፊት በሽታዎችን በወቅቱ መታከም ዋንኞቹ የእግራችንን ጤና መጠበቂያ መንገዶች ናቸው፡፡

* በዚህ ህመም የታመመ ሰው ህክምና በቶሎ ማግኘት አለባለው የተባለ ሲሆ ይህ ሳይሆን ከቀረ ግን አንዱን አሊያም ሁለቱንም እግሮቻችንን ሊያዝላቸው አሊያም ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ ሊያደርጋቸው ይችላል ተብሏል ።

በልዑል ወልዴ

ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply