
የኦህዴድ መራሹ ስርዓት በአማራ ላይ በከፈተው ጦርነት በትንሹ የአምስት ንፁኃን ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ! ግንቦት 11 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋሮቢት ዙሪያ ራሳ ተብሎ ከሚጠራ ስፍራ ረቡዕ ግንቦት 9 ቀን 2015 ዓ.ም ፋኖን ለማጥፋት በሚል በስርዓቱ ታጣቂዎች በተደረገው ግልፅ ጦርነት በትንሹ የአምስት ሰዎች ንፁኃን ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ። በሸዋሮቢት ዙሪያ እና አካባቢዋ በተደረገው በዚህ ውጊያ ንፁሃን ዜጎች የሞት ሰለባ ሁነዋል የተባለ ሲሆን፤ ሰላማዊ ሰዎች አካባቢያቸውን ለቀው መሄዳቸው ነው የተገለጸው፡፡ በዚህ በጦርነት በተከፈተው ውጊያ የኦነግ ሸኔ አባላት ከመከላከያ ጋር በማበር ተሳትፈዋል የሚሉት ነዋሪዎቹ፤ በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን እና በሰሜን ሸዋ ዞን መካከል በሚገኙ አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ ውጥረት መንገሱን ተናግረዋል። በአካባቢው ሲካሄድ በነበረው የተኩስ ልውውጥ የከባድ መሳሪያ ድምፅ ይሰማ እንደነበርም ነው ለማወቅ የተቻለው፡፡ በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን እና በሰሜን ሸዋ ዞን አካባቢዎች በሚከሰቱ ግጭቶች በየወቅቱ የሰው ሕይወት እየጠፋ፣ ቤት እየተቃጠለ፣ ሃብት ንብረት እየወደመ የቀጠለ ቢሆንም፣ የፌደራል መንግሥቱ በዘላቂነት ሊያስቆመው ባልመቻሉ በርካታ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲሰደዱ እንዳስገደዳቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ በዚህ ዓመት ብቻ ከሦስት ጊዜ በላይ በአካባቢው ጦርነት ተካሂዶበታል የሚሉት የራሳ እና ግድም ነዋሪዎች፤ በአካባቢው ሰላም ያስከብራሉ ተብለው የተመደቡ የአገር መከላከያ ሰራዊት የንፁሃንን ሕይወት ከመጠበቅ ይልቅ ንፁሀንን በከባድ መሳሪያ እየደበደበ ነው ብለዋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post