የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ ያሰማራው በእስካቫተር የሚታገዘው አፍራሽ ግብረ ኃይል ሸገር ሲቲ ኩራ ጅዳ ብሎ በሚጠራው ክ/ከተማ አርባ አራት ማዞሪያ በወታደር ሰፈር የዜጎችን ቤት ማፍረሱን አጠና…

የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ ያሰማራው በእስካቫተር የሚታገዘው አፍራሽ ግብረ ኃይል ሸገር ሲቲ ኩራ ጅዳ ብሎ በሚጠራው ክ/ከተማ አርባ አራት ማዞሪያ በወታደር ሰፈር የዜጎችን ቤት ማፍረሱን አጠናክሮ ቀጥሏል። መጋቢት 18/2015 ከረፋ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 19 ቀን 2015 ዓ/ም … አዲስ አበባ ሸዋ የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ ያሰማራው በእስካቫተር የሚታገዘው አፍራሽ ግብረ ኃይል ሸገር ሲቲ ኩራ ጅዳ ብሎ በሚጠራው ክ/ከተማ አርባ አራት ማዞሪያ በወታደር ሰፈር የዜጎችን ቤት ማፍረሱን አጠናክሮ ስለመቀጠሉ የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች ናቸው። “አገዛዙ ጠቡን ከህዝብ ጋር ካደረገ ቆይቷል!” የሚሉት የአሚማ ምንጮች በአበባ ልማት ለገኦላ አካባቢ ከየካቲት 11/2015 ጀምሮ ከ12,000 በላይ አባዎራ ቤቶችን ስለማፍረሱ ገልጸዋል። ከመጋቢት 18/2015 ከረፋዱ 4 ሰዓት ጀምሮ ደግሞ በቀደመ ስሙ ሰንዳፋ በኬ 03 ቀበሌ በአዲሱ አጠራር ሸገር ሲቲ ኩራ ጅዳ ክ/ከተማ አርባ አራት ማዞሪያ ወታደር ሰፈርን እያፈረሰ ስለመሆኑ ተገልጧል። በዚህ የማፍረስ ዘመቻም 360 የሚሆኑ አባዎራዎች የሚኖርበት ሰፈር እየፈረሰ ይገኛል ብለዋል። በወታደር ሰፈር ቤት ገዝቶ መኖር ከጀመረ 17 ዓመት እንደሆነው የገለጸው ሌላኛው ቤታቸው የፈረሰባቸው ነዋሪ የኦሮሞ ተወላጅ ከሆኑት ወታደሮች ውጭ የሌሎች ቤት እንዲፈርስ መደረጉን ተናግረዋል። “መንግስት እያፈረሰው መንግስት ይድረስልን አልልም” ያሉት ምንጫችን የኢትዮጵያ ህዝብ እየደረሰብን ያለውን የግፍ ግፍ እንዲሰማልን እንፈልጋለን ሲሉ ተማጽነዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply