#የኦህዴድ ክንፍ የሆኑ የብአዴን አመራሮች የአማራ ልዩሃይልን እና የአማራ ፋኖን ለማጋጨት ሴራ እየጠነሰሱ መሆኑ ተገለፀ! መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የኦህዴድ ክንፍ የሆ…

#የኦህዴድ ክንፍ የሆኑ የብአዴን አመራሮች የአማራ ልዩሃይልን እና የአማራ ፋኖን ለማጋጨት ሴራ እየጠነሰሱ መሆኑ ተገለፀ! መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የኦህዴድ ክንፍ የሆኑ የብአዴን አመራሮች በልዩሃይሎች እና በፋኖዎች መካከል ግጭት ለማሰነሳት ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ በመውረድ ሴራ እየጠነሰሱ ይገኛሉ ሲሉ የአማራ ልዩሃይል አባላት ተናግረዋል። መላላክን እንደ ጀብድ በመውሰድ የአማራን ህዝብ በመርሳት የኦህዴድ ክንፍ የሆኑ የብአዴን አመራሮች በአንድ ክልል የሚኖሩ ወንድማማቾችን ለመለያየት ብሎም እርስ በርሳቸው እንዲገዳደሉ ለማድረግ ደፋ ቀና እያለ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል። ከዚህ በፊት ልዩሃይሎችን እና ፋኖዎችን ለመለያየት በተቀናጀ መልኩ ከፍተኛ ስራ ሲሰራ የቆየ ቢሆንም በተደጋጋሚ ሴራው ከሽፎበት ሳይሳካለት የቀረው የኦህዴድ ተላላኪው ብአዴን አሁንም አደገኛ የሆነ ሴራ እየሸረበ ይገኛል ብለዋል። ሃገራችን የህልውና አደጋ ውስጥ በገባችበት ወቅት የአማራ ልዩሃይል እና የአማራ ፋኖ ከሃገር መከላከያ ሰራዊቱ ጋር እኩል በመሰለፍ መስዋዕትነት በመክፈል ከፍተኛ ድል ማስመዝገቡ ይታወሳል።ነገር ግን በተቃራኒው የኦህዴድ ክንፍ የሆኑ የብአዴን አመራሮች ፋኖን በተደጋጋሚ ጥላሸት በመቀባት ከወንድሞቹ ለመለየት ከፍተኛ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። በመጨረሻም የአማራ ልዩሃይልን እና የአማራ ፋኖን መለያየት ስለማይቻል እነዚህ የብአዴን አመራሮች ከዚህ እኩይ ተግባራቸው እንዲታቀቡ ሲሉ የልዩሃይል አባላቶች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ፎቶ:- ከማህደር “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply