የኦሎምፒክ አትሌቶች ተለይተዋል! ኢትዮጵያን በቀጣዩ የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በ10,000 ሜትር የሚወክሉ አትሌቶችን ለመለየት እንዲሁም የኦሎምፒክ ሚኒማ ለማሟላት የሙከራ ውድድሮች በስፔን ኔ…

የኦሎምፒክ አትሌቶች ተለይተዋል!

ኢትዮጵያን በቀጣዩ የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በ10,000 ሜትር የሚወክሉ አትሌቶችን ለመለየት እንዲሁም የኦሎምፒክ ሚኒማ ለማሟላት የሙከራ ውድድሮች በስፔን ኔርጃ ተካሂደዋል።

በ800ሜ ወንዶች በተደረገው የኦሎምፒክ ሚኒማ ማሟያ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች 1:44:70 የሆነውን የኦሎምፒክ ሚኒማ ማሟላት ሳይችሉ ቀርተዋል።

በኦሎምፒክ 10000ሜ ሴቶች ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶችን ለመለየ በተደረገው ውድድር ፎትዬን ተስፋይ ፣ ፅጌ ገብረሰላማ እና እጅጋየሁ ታዬ ተከታትለው በመግባት ማሸነፍ ችለዋል።

በወንዶች 10000ሜ ውድድር ዮሚፍ ቀጄልቻ ፣ በሪሁ አረጋዊ እና ሰለሞን ባረጋ ተከታትለው በመግባት ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል።

በ1500ሜ ወንዶች ሚኒማ ማሟያ ውድድር አትሌት አበዲሳ ፈይሳ እና ሳሙኤል ተፈራ 3:33:50 የሆነውን የኦሎምፒክ ሚኒማ በሟሟላት አንደኛ እና ሁለተኛ ሆነው አጠናቀዋል።

በጋዲሳ መገርሳ

ሰኔ 08 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply