የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች በቡኖ በደሌ በጅምላ ታሥረዋል፤ ፍርድ ቤትም እየቀረቡ አይደለም። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 12 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በ…

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች በቡኖ በደሌ በጅምላ ታሥረዋል፤ ፍርድ ቤትም እየቀረቡ አይደለም። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 12 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚያ ክልል በቡኖ በደሌ ዞን አሁንም በኦርቶዶክሳዊነታቸው ብቻ ቢያንስ 13 ምእመናን እና የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች በእስር ላይ ናቸው። እነዚህም:_ 1) ምትኩ በክሳ፣ 2) አዲሱ ታደሰ፣ 3) ፍቅሩ ሰውነት፣ 4) ኤፍሬም ረዳ፣ 5) ገረመው እንየው፣ 6) ዘላለም በላይነህ፣ 7) አቡሽ ጸጋ፣ 8 መለሰ ንጋቱ፣ 9) ታምራት ጥላሁን፣ 10) አሸናፊ ገ/መስቀል፣ 11) ደሳለኝ ጸጋ፣ 12) የኔነሽ ዘላለም እና 13) ኪዳኔ ሽብሩ ናቸው። እስረኞቹ ከታሰሩ ከሰባት እስከ አሥራ አንድ ቀናት ቢሆናቸውም አንዳቸውም እስካሁን ፍርድ ቤት አልቀረቡም። የታሰሩትም ግማሹን ከቤተ ክርስቲያን በጅምላ በመታፈስ ሲሆን የተቀሩት ደግሞ ያለአግባብ የታሰሩትን ኦርቶዶክሳዊያን ክርስቲያኖችን ሊጠይቁ በሄዱበት ወቅት በዚያው ተይዘው መግባታቸው ታውቋል። አደባባይ ሚዲያ እንዳጋራው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply