
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አገልጋዮችን አፈና ዛሬም እንደቀጠለ መሆኑ ተነገረ። ግንቦት 16፥2015 ዓም አሻራ ሚዲያ ፥ ባህር ዳር እሁድ እለት በማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ መግለጫ ተነበበ።መግለጫው የተነበበት ጣቢያ ወዲያው ተዘጋ።መግለጫውን ያነበቡት ወንድሞች ታፈኑ።መሃል ላይ የሚታዩትን መ/ር ተሾመ በየነ ከፌዴራል ፖሊስ እስከ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አፈላለግን ግን የሉም። በዳር ላይ የሚታዩት ቀሲስ አክሊለ ዛሬ በአራዳ ፍ/ቤት ቀረቡ።ፖሊስ ቀሲስን ‘ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት ህገመንግስታዊ ስርአቱን በሃይል ለመናድ በመሞከር የጦር መሳሪያ በማስታጠቅ የተለያዩ የፖለቲካ ሃይሎችን ወታደራዊ ስልጠና እንዲያገኙ በማድረግ እና በሃገር ማፍረስ ሴራዎች ጠርጥሬያቸዋለሁ!!’ ብሏል። ፍርድቤት ለምርመራ 12 ቀናት ፈቅዷል። አሁን ከፍርድቤት ወጥተን መ/ር ተሾመ በየነን እና ዲያቆን ዮናስን እያፈላለግን ነው። ሶስት ቀናት የት እንዳሉ እንኳን የሚነግር የለም። መረጃው የህግ ባለሙያው አንዷለም ቡክቶ ነው! ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post